Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ሰሙኑን በጎንደር ከተማ ነዋሪ የሆነችው እና የተለያዩ ተቋማትን ለማቃጠል ስትሞክር ተያዘች የተባለችው ተጠርጣሪ ተለቀቀች።

0 1,327

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ሳያጠሩ ሰውን መወንጀል ወንጀል ነው!

ሰሙኑን በጎንደር ከተማ ነዋሪ የሆነችን ሴት የመንግስት ተቋማትን ልታቃጥል ስትል ተያዘች የሚል ዜና በማህበራዊ ድህረገጽ ሲሰራጭ ተመልክተናል። በሌላ በኩል ከተቃዋሚዎች ጎራም ተጠርጣሪዋ ወያነ ንብረት እንድታቃጥል የተላከች የሚል የተዛባ መረጃ ከንብረት ተቆርቋሪነት ሳይሆን በሬ ወለደ አሉባልታ ተሰራጭቷል። በተጠርጣሪዋ ላይ እንግልት ለመድረሱ የተለያዩ ማስረጃዎችም ተገኝተዋል።በተግባርም ታይተዋል ለአብነት ያህል ከመኖርያ ቤቷ ተጠርጣሪ መሆና ተነግሯት ፖሊስ ለምርመራ እንደሚፈልጋት ተነግራት ከቤቷ የተወሰደችን ግለሰብ ወንጀለኛ መሆንዋ እንኳን በህግ አካላት ሳይረጋገጥ በየአደባባዩ በማዞርና ወንጀል ልትፈጽም ስትል እጅ ከፍንጅ የተያዘች ማስመሰሉ በግለሰባ የሚፈጥረው የስነልቦና ችግር ሆነ ከማህበረሰብ ዘንድ የሚፈጠርባትን መገለል ለመቋቋም ሆነ እውነታው ለማስረዳት የሚፈጥረው ጫና ከባድ ያደርገዋል። ይህንን ድርጊት የፈጸሙት የፀጥታ አካላት እነማን ናቸው? ከቅርብ ግዜ ወዲህ በሀገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች ተቀስቅሶ በነበረ ግጭት መሠረታቸው በውጭ ሀገራት ያደረጉ ፀረ ሠላምና ፀረ ሰላም ሀይሎች ሰለባ ከነበሩት ወጣቶችና ነዋሪዎች ባሻገር የተወሰኑ የፀጥታ ሀይል አባላትም ተሳታፊዎች ነበሩ ምንም እንኳን የጥፋተኝነት ውሳኔ በህግ አካላት የሚወሰን ቢሆንም ነገሮች ተጣርተው ጥፋተኛ ናቸው/ አይደለም የሚለው የሚወሰን ቢሆንም ሰብአዊ መብታቸው ግን አይጣስም። በህግ ደረጃ ሲታይም ይህ ድርጊት እነዚህን የፀጥታ አካላት በህግ የሚያስጠይቅ በመሆኑ ምክንያት በህግ መጠየቅ ይኖርባቸዋል። ከዚህ ባሻገር በክልል ይሁን በፌደራል ሴቶች እና ህጻናት ይህን ድርጊት ሊያወግዙና ድርጊቱን የፈጸሙ አካላት በህግ እንዲጠየቁና ለሌላው አስተማሪ የሆነ ቅጣት እንዲያገኙ የበኩላቸውን ጥረት ማድረግ ይገባቸዋል። በሀገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች በሴቶች ላይ የሚደርሱ ስነልቦናዊ እና አካላዊ ጥቃቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከቱ መጥተዋል ለዚህ ችግር መስፋፋት እንደ ምክንያት ሊጠቀስ የሚችለው የህግ መላላት ሲሆን ይኸው የህግ፡መላላት በህግ አስከባሪዎች ዘንድም ህግ እንዲጣስ ምክንያት ሆኗል። ከሳምንት እንግልትና መጉላላት ቡሀላም ሰሙኑን በጎንደር ከተማ ነዋሪ የሆነችው እና የተለያዩ ተቋማትን ለማቃጠል ስትሞክር ተያዘች የተባለችው ተጠርጣሪ የተለቀቀች ሲሆን ለመለቀቋ ምክንያት የሆነው የክልሉ ፖሊስ ባደረገው ማጣራት ከተጠረጠረችበት ወንጀል ጋር ምንም አይነት ንኪኪ እንደሌላት እና ፈፅሞ ግኑኝነት እንደሌላት በመረጋገጡ ነው። ለአብነት ያህል ይህን ብናነሳም በተለያዩ ቦታዎች የሚፈጠሩ የመብት ጥሰቶች አሉ።ህግን እየጣሱ ህግ አስከባሪነት ስለሌለ ህግ የጣሱ አካላት በህግ መጠየቅ አለባቸው።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy