Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በም/ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ጉዳዮች ክላስተር አስተባባሪና የመገናኛና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር #ዶክተር_ደብረፅዮን_ገብረሚካኤል ከተለያዩ ድህረ ገፆች ለተውጣጡ ጋዜጠኞች በወቅታዊ ሁኔታ ዙርያ በትናንትናው እለት ቃለምልልስ አድርገዋል።

0 491

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በም/ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ጉዳዮች ክላስተር አስተባባሪና የመገናኛና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር
#ዶክተር_ደብረፅዮን_ገብረሚካኤል
ከተለያዩ ድህረ ገፆች ለተውጣጡ ጋዜጠኞች በወቅታዊ ሁኔታ ዙርያ በትናንትናው እለት ቃለምልልስ አድርገዋል።
ለዶክተር ደብረጽዮን ከቀረቡት ጥያቄዎች መካከልም *
በክልሎች እየተፈጠሩ ስላሉ ግጭቶች በተመለከተ ሲሆን ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ግጭቶቹ እየተነሱ ያሉት መንግስት መፍታት እያለበት ባልተፈቱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ምክንያት በማድረግ የውጭ ኃይሎች ገብተው በማቀጣጠላቸው በመሆኑ እና እነዚህ በኢትዮጵያዊነት የሚነግዱ ህዝብን የካዱ ኃይሎች እንቅስቃሴ መንግስት በሚገባ ከማወቁም ባሻገር መረጃ ብቻ ሳይሆን ማስረጃም እንዳለ በመግለፅ ለዚህ የሚሆን ስራ እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል የሚታዩ ችግሮችን እና የህብረተሰቡን ጥያቄ ለመመለስ ይቻል ዘንድ መንግስት ውስጥ እጥረቶቹ ላይ አተኩሮ መስራት እንዳለበት አምኖ እንደሚሰራና የተነሱ ችግሮች በመፍታት እና በተገቢ መልኩ በማስተካከል የውጭ ሀይሎቹ መግቢያ ቀዳዳ እንዳይኖራቸው እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች በአንድ ብሄር ላይ ስለተከሰተው ግድያ፣ንብረት ማውደምና ወደ ጎረቤት ስደት አስመልክቶ ለተነሳው ሀሳብም በአማራ ክልል የተፈጠረው ችግር የህዝብ ለህዝብ ጉዳይ ያልሆነ ሌሎች ጥፋቶችን በመፈጸም የፌደራል ስርአቱን ለመናድ በሌሎች ሀይሎች የተቀሰቀሰ መሆኑና የአማራ ክልል ህዝብም ሆነ ብሎ በትግራይ ህዝብ ላይ ችግር አለመፍጠሩን እና የክልሉ ህዝብ ችግሮች እንዳይባባሱ የመከላከል ስራ እየሠራ መሆኑንም አውስተዋል። ኢህአዴግ በቅርቡ ስላካሄደው ግምገማ እና ቀጣይ አቅጣጫ አስመልክቶ ለተነሳው ጥያቄ ዶ/ ር ደብረፅዮን ሲመልሱ ኢህአዴግ በስራ አሰፈጻሚ ደረጃና በም/ቤት ያያቸውን ጉዳዮች በብሄራዊ ድርጅት በጥልቀት ከማየት ባሻገር በቀጣይ ደግሞ አስከታችኛው መዋቅር ደረስ ተከታታይ የህዝብ መድረኮች በመፍጠርና ጎን ለጎንም በመስሪያ ቤቶች በትምህርት ተቋማት ሰፉፊ መድረኮችን በመፍጠር በችግሩ ላይና በመፍትሄው ላይ የጋራ መግባባት ይደረሳል ፡፡በተጨማሪም በየግዜው የሚወስዳቸውን እርምጃዎች ለህዝቡ በፍጥነት የማሳወቅ ስራ እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡ በተለያዩ ማህበራዊ ድህረ ገፆች ስለሚነሱ መሠረተ ቢስ አሉባልታዎች እና አሉባልታ ከማጋለጥና እውነተኛ መረጃ ለህዝብ ከማዳረስ አኳያ መደረግ ስላለበት ነገር ተጠይቀውም ይህን ብለዋል። ” ሶሻል ሚዲያው የፅንፈኛው ነፃ መሬት ሊሆን አይገባም ማንኛውም ሀገር ወዳድ ዜጋ አንድ መስመርም ቢሆን ስለሀገሩ ሰላም በመግለፅ ሊሳተፍበት የሚገባበት ቦታ ነው መንግስትም በግምገማው እደከፍተት ካያቸው መስኮች አንዱ ነው በቀጣይም አጠናክሮ የሚሰራበት ለመዘላለፊያነት ሳይሆን እውነቱን የሚያስረዳበት አንዱ ክንፍ ይሆናል።ብለዋል በመጨረሻም ከቅርብ ግዜ ወዲህ በስማቸው በተከፈተ የፌስ ቡክ ገጽ ስለሚሰራጩ ዜናዎች ይህን ብለዋል። “በስሜ በተከፈተ የሀሰት የፌስቡክ ገጽ እየተላለፈ ያለው መልእክት ከሽፍታ እንጂ ሐላፊነት ከሚሰማው የመንግስት ሐላፊ የሚጠበቅ አይደለም። ይህን ደግሞ ህዝብ መዝኖ እንደሚረዳና የፌስ ቡክ ገፅ እንደሌላቸው ገልጸዋል።
 #የበለጸገች_ ኢትዮጵያ
ነሀሴ 2008 ዓ/ ም

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy