አንዳንድ ልጆች ኤድስን ለመከላከል የሚያስችል ተፈጥሮ እንዳላቸው ተመራማሪዎች ገለፁ
መስከረም 19 ፣2009
ሳይንስ ትራንዚሽን ሜዲስን የተባለ ተቋም በደቡብ አፍሪካ እንዳጠናው ከ10 ህጻናት አንዳቸው ኤች አይ ቪ ኤድስን ለመከላከል የሚያስችል ተፈጥሮ እንዳላቸው አመላከተ፡፡
ጥናቱ እንደሚያሳየው የመከላከያ ሥርዓታቸው በሰውነታቸው ውስጥ ያለውን እንቅስቃሴ በመቆጣጠር አላስፈላጊ ነገሮችን ወደ ውጭ እንዲወጡ ያደርጋል፡፡
በጥናቱ 170 ቫይረሱ በደማቸው የሚገኝባቸው ህጻናት መካተታቸውን ዘገባው ያስረዳል፡፡
ግኝቱ ኤች አይ ቪ ኤድስን ለመከላከል አቅም ላይ የተመሰረተ ሕክምና ለማድረግ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡
ምንጭ፡- ቢቢሲ