የአለም አቀፍ ግዙፍ ወርቅ አምራቾች ኢትዮጵያን መዳረሻ ሊያደርጉ ነው
በአለም ደረጃ በወርቅ ፍለጋ ላይ የተሰማራው ግዙፍ የወርቅ አምራች ኩባንያ ኒውማውንት የወርቅ ፍለጋውን ወደ ኢትዮጵያ ሊያስፋፋ መሆኑን የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ጎልድ በርግ ለሮይተርስ ገልጸዋል፡፡ኩባንያው ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ኮትዲቫር፣ ክዊንስ ላንድና አውስተራሊያ ለተጨማሪ ወርቅ ፍለጋ የመረጣቸው ሀገራት ናቸው፡፡
የአለም አቀፍ ግዙፍ ወርቅ አምራቾች ትኩረታቸውን ባሉበት አከባቢ ማድረጋቸው ከወጪ አንጻር አዋጭ ቢሆንም ከምርታማነት አንጻር የማይመከር መሆኑን የሮይተርስ ዘገባ ያስረዳል፡፡ ይህን ተከትሎ በቀጣይ 3 አመታት የወርቅ ምርት 9 በመቶ ሊቀንስ እንደሚችል ተተንብይዋል፡፡