Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የኦሮሚያና ደቡብ ክልልሎች ከ8ሺህ በላይ ለሚሆኑ የህግ ታራሚዎች ምህረት አደረጉ

0 574

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የኦሮሚያና ደቡብ ክልልሎች ከ8ሺህ በላይ ለሚሆኑ የህግ ታራሚዎች ምህረት አደረጉ

ጳጉሜ 4፣2008

የኦሮሚያ እና  ደቡብ  ክልሎች መጪውን አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ ለ8 ሺህ ላይ የህግ ታራሚዎች ምህረት ማድርጋቸንውን አስታወቁ፡፡

በኦሮሚያ ክልል ከ5ሺ 4 መቶ በላይ ታራሚዎቹ ምህረት የተደረገላቸው በማረሚያ ቤት ቆይታቸው ጥሩ ስነ ምግባር ያላቸው እና የእርምት ቆይታቸውን በግማሽ ያጠናቀቁ ናቸው ተብሏል፡፡

በሙስና፣ በሽብርተኝነት፣ በሰው መግደል እና አስገድዶ መድፈር  የተፈረደባቸው ታራሚዎች በምህረቱ አልተካተቱም፡፡

ምህርት የተደረገላቸው ታራሚዎች ወደ ህብረተሰቡ ሲቀላቀሉ ለሀገሪቱ ሰላም እና ዕድገት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ ማቅረባቸውን ሪፖርተራችን ሙባረክ ሙሃመድ ዘግቧል።

በተያያዘ የደቡብ ክልል መንግሥት አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ከ3 ሺህ ለሚበልጡ የህግ ታራሚዎች ምህረት ማድረጉን ገልጿል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደሴ ዳልኬ ማምሻውን ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ይቅርታ የተደረገላቸው የህግ ታራሚዎች በተለያዩ ወንጄሎች በፍርድ ቤት ውሳኔ የተሰጣቸው ናቸው፡፡

ይቅርታ የተደረገላቸው ታራሚዎች በቆይታቸው በፈጸሙት ወንጀል የተጸጸቱ፣ ትምህርት ያገኙና የበደሉትን ህብረተሰብ ለመካስ ዝግጁ መሆናቸው መረጋገጡንም ርዕሰ  መስተዳድሩ አመልክተዋል፡፡

የህግ ታራሚዎቹ ወደ ህብረተሰቡ ሲቀላቀሉ የበለጠ ውጤታማ ሆነው ህብረተሰቡን መካስ እንደሚኖርባቸውም ርዕሰ መስተዳድሩ አስገንዝበው፤ ህብረተሰቡም በፍቅር እንዲቀበላቸው ጥሪ አስተላለፏል ሲል ኢዜአ ዘግቧል ።

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy