Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ጠ/ሚ ኃይለማሪያም የማህበራዊ ትስስር ድረ ገጾች የጥላቻና አለመቻቻል አመለካከቶች ማሰራጫነት እየዋሉ ነው ሲሉ ተቹ

0 746

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ጠ/ሚ ኃይለማሪያም የማህበራዊ ትስስር ድረ ገጾች የጥላቻና አለመቻቻል አመለካከቶች ማሰራጫነት እየዋሉ ነው ሲሉ ተቹ

ጠ/ሚ ኃይለማሪያም የማህበራዊ ትስስር ድረ ገጾች የጥላቻና አለመቻቻል አመለካከቶች ማሰራጫነት እየዋሉ ነው ሲሉ ተቹ

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ የማህበራዊ ትስስር ድረ ገጾች የጥላቻና አለመቻቻል አመለካከቶች ማሰራጫነት እየዋሉ ነው ሲሉ ተችተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተባበሩት መንግስታት ድርጅ 71ኛው የመሪዎች ጉባዔ ላይ ባደረጉት ንግግር፥ የማህበራዊ ትስስር ድረ ገጾች በቀላሉ መረጃን ለማስተላለፍ እና ለመቀባበል እየተጫወቱት ያለው ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል።

ሆኖም ግን አሁን አሁን ላልተገባ አላማ እየዋሉ ይገኛሉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ በዜጎችና በአገር ላይ የሚያሳድረው አሉታዊ ተጽዕኖ በቀላሉ ልንተወው የሚገባ አይደለም ሲሉም አሳስበዋል።

የተሳሳቱ መረጃዎች በማህበራዊ ትስስር ድረ ገጾች አማካኝነት በቀላሉ በዓለም ዙሪያ ሲተላለፉ ይስተዋላል፤ ይህም በርካቶች በተለይም ወጣቱን ትውልድ ወደ ተሳሳት ተግባር እንዲገባ እያደረገ ነውም ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ጽንፈኞች እና ጸረ ሰላም ሀይሎች ያለምንም ገደብ የጥላቻ እና አለመቻቻል መልእክታቸውን በማህበራዊ ትስስር ድረ ገጾች ሲያስተላለፍ ይስተዋላል ሲሉም ተናግረዋል።
በማኅበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ ጽንፈኛ መረጃዎች በሕዝቦች ዘንድ ያለውን ሚዛናዊ አስተሳሰብ እያዛባ በመሆኑ ትኩረት ሊሰጠው ይገባልም ብለዋል።

የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ሲባል በሰዎችና በቡድን ተደራጅተው የተነሱ የሕዝብ ጥያቄዎችን መነሻ በማድረግ በአገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች ከተፈጠሩ አለመረጋጋቶች ውጪ የሚወራውን ያህል የተጋነነ ችግር በኢትዮዽያ አለመኖሩን አስረድተዋል።

ሀገሪቱ በዚህ አስቸጋሪና ቀላል መፍትሄ በማይገኝላቸው የደህንነት ችግሮች ውስጥ ሆና እንኳ የመንግስታቱን ድርጅት ቀጣይ የልማት ግቦች ተግባራዊ ለማድረግ ጥረት ውስጥ ትገኛለች ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

ኢትዮጵያ ድህነትን ለማሸነፍ በምታደርገው ጥረት ውስጥ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ከሀገሪቱ ህዝቦች ጋር በመመካከር ትፈታለች ሲሉም ተናግረዋል።

ሀገሪቱ የጀመረችው የልማት ጉዞ ስኬትን እያስመዘገበ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ለዚህ ምስክር ሩቅ መሄድ ሳይጠበቅብን ባለፈው ዓመት ያጋጠማትን የኤል ኒኖ ችግር በራሷ አቅም መወጣት የቻለችበትን መንገድ በማሳያነት አንስተዋል።

ኢትዮጵያም ያጋጠሟትን ችግሮች በቀላሉ አትመለከትም፤ በተደራጀና በተቀናጀ መንገድ ምላሽ ለመስጠት በአካባቢያችንና ከአካባቢያችን ውጭ ካሉ አገራት ጋር ግንኙነት በመፍጠር ለችግሮች ዘላቂ ምላሽ ለመስጠት እንሰራለን ሲሉም ተናግረዋል።
ምንጭ፦ www.un.org

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy