Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

“በምእራብ አርሲ ፀረ-ሰላም ሀይሎች በእምነትና ማንነት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ፈፅመዋል” – የዞኑ አስተዳደር

0 807

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

“በምእራብ አርሲ ፀረ-ሰላም ሀይሎች በእምነትና ማንነት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ፈፅመዋል” – የዞኑ አስተዳደር

“በምእራብ አርሲ ፀረ-ሰላም ሀይሎች በእምነትና ማንነት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ፈፅመዋል” - የዞኑ አስተዳደር

በኦሮሚያ ክልል ግጭት ከሚታዩባቸው ዞኖች አንዱ በሆነው ምእራብ አርሲ ዞን ፀረ ሰላም ሀይሎች ግጭቱን በመጠቀም ህዝብን ከህዝብ በዘር እና በሀይማኖት ማንነትን በመለየት ጥቃት መፈፀማቸውን የዞኑ አስተዳደር እና ፀጥታ መምርያ አስታወቀ።

በዞኑ የታየው የፀጥታ ችግር በአንዳንድ የኦነግ አላማ አራማጆች ቀስቃሽነት የተከወኑ እና ህዝብን ከህዝብ ማጋጨትን ታሳቢ ያደረጉ መሆናቸውንም ነው መምርያው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የገለጸው።

በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዲ በኢሬቻ በዓል ላይ በመገፋፋትና መተፋፈን ምክንያት የሰው ህይወት በጠፋ ማግስት አንዳንድ ወገኖች ህዝቡን በአሉባልታ በመቀስቀስ በኦሮሚያ አንዳንድ አከባቢዎች ግጭቶች ተከስተዋል።

ከእነዚህ አከባቢዎች አንዱ በሆነው ምእራብ አርሲ ዞን ግጭቱ ሰፋ ባለ መልኩ መታየቱን ነው የዞኑ አስተዳደር እና ፀጥታ መምሪያ ሃላፊ የሚናገሩት።

በተለይም በአርሲ ነገሌ፣ ሻላ እና አሳሳ ወረዳዎች፣ በኮፈሌ እንዲሁም በተወሰኑ መልኩ በዶዶላ አከባቢዎች ግጭቱ ተከስቷል።

ግጭቱ በተጠቀሱት አካባቢዎች ቢነሳም አሁን ላይ በህብረሰተቡ እና በአካባቢው አባቶች ትብብር ረገብ ማለቱን የመምርያው ሀላፊ አቶ ያሲን ገርጁ ተናግረዋል።

ሁኖም ችግሩ በሁለት ወረዳዎች ላይ አሁንም መኖሩን ነው የጠቀሱት።

በቢሾፍቱ የደረሰውን እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም አሸባሪው ኦነግ በተለያዩ ማህበራዊ ድረ ገፆች ቅስቀሳዎችን በማድረግ ለአመጽ እንዲነሳሱ ድርጓል ብለዋል።

ይህን ተከትሎም የአሸባሪውን አላማ ለማራመድ የሚፈልጉ ግለሰቦች ግጭቱን እንደቀሰቀሱት ሃላፊው ይናገራሉ።

እነዚህ ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ ተቋውሞ መልዕክት የተንፀባረቀባቸው ሳይሆኑ፥ በዋናነት የአካባቢው ማህበረሰብ የሚገለገልባቸውን መሰረተ ልማቶች ማውደም ላይ ያነጣጠሩ እንደነበሩ ነው የተናገሩት።

ግጭቱ በተቀሰቀሱባቸው ወረዳዎች እና ቀበሌዎች የሚገኙ ፅህፈት ቤቶች፣ የአርሶ አደር ማሰልጠኛ ተቋማት እና የጤና ኬላዎች ላይ ጥቃት ተፈፅሞባቸዋል ብለዋል።

“ግጭቱ የኦሮሚያን እና የዞኑን ልማት ለማደናቀፍ ሆነ ተብሎ በታጠቁ ፀረ ሰላም ሃይሎች እና ግጭቱን ተገን በማድረግ በግል ለመጠቀም በሚንቀሳቀሱ ሃይሎች የተከወነ ነው” ሲሉ ሀላፊው አንስተዋል።

በዚህ መሃልም ለዘመናት በአብሮነት እና በመቻቻል የኖረውን ህዝብ ለማለያየት ብሎም የኦሮሞን አብሮ የመኖር ታሪክ ለማጠልሸት ታሳቢ ያደረጉ እንቅስቃሴዎች እንደነበሩ አንስተዋል።

በግጭቱም ማንነትን እና ሀይማኖትን በመለየት የግለሰቦችን መኖሪያ ቤቶች እስከ ማቃጠል የደረሰ እንደነበር ነግረውናል።

እምነትን በመለየትም የ40 ቤተሰቦችን መኖሪያ ቤት ያቃጠሉ ሲሆን፥ እነዚህ ቤታቸው የተቃጠለባቸው ቤተሰቦች በቤተ ክርስቲያን ተጠልለው ይገኛሉም ነው ያሉት።

ግጭቱ በዋናነት ተቀስቅሶባቸው በነበሩ ወረዳዎች ላይ የፀጥታ ሃይሉ ህብረተሰቡን እና የአካባቢውን አባቶች በማቀናጀት ለማብረድ ተችሏል የሚሉት አቶ ያሲን፥ አሁን ላይ ከሁለት ወረዳዎች ውጭ አከባቢው መረጋጋቱን ተናግረዋል።

ዞኑ በቀጣይም ከአካባቢው ህብረተሰብ እና አባቶች ጋር በመነጋገር የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት እና በቀጣይ የዞኑን ሰላም ለማስጠበቅ እንደሚሰራም ሀላፊው ተናግረዋል።
በፍቅሩ ወልዱ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy