Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኢትዮጵያን የማዳከምና የመበታተን ዓላማ ያነገቡ ሃይሎች ቅዠት

1 793

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኢትዮጵያን የማዳከምና የመበታተን ዓላማ ያነገቡ ሃይሎች ቅዠት
• የግብፅ አክራሪ ሃይሎች ህልም
ያለፉት በ100ዎች የሚቆጠሩ ዓመታት ተሞክሮ እንደሚነግረን የደኸየችና የተዳከመች ኢትዮጵያ እስካለች ድረስ ብቻ ነው የናይል ውሃ እንደፈለግን የምንጠቀምበት፣ ትርፍ ውሃ ካለም ለአረብ አገራትና ለእስራኤል በመሸጥም ገቢ ልናገኝበት የምንችለው፡፡ ጠንካራና የበለፀገች ኢትዮጵያ ካለች ግን ይህ ጥቅም ሳንወድ ትጋራናለች፡፡ ስለዚ የደኸየችና የተዳከመች ኢትዮጵያ እንድትሆን ጠንክረን መስራት አለብን
• የሻዕብያ ስርዓት ህልም
የ25 ዓመት ተሞክሮ እንደሚያሳየው የደኸየችና የተዳከመች ኢትዮጵያ እስካለች ድረስ ብቻ ነው በኢትዮጵያ ውስጥ ገብተን የኢትዮጵያ ሃብት እንደፈለግን እናተራምሳለን፡፡ ጠንካራና የበለፀገች ኢትዮጵያ ካለች ግን ይህ ጥቅም ይቀርብናል፡፡ ስለዚ የደኸየችና የተዳከመች ኢትዮጵያ እንድትኖር አንድነትም ነፃነትም ከሚመኙ ሃይሎች ጠንክረን መስራት አለብን፡፡ በመጨረሻም ምን ማድረግ እንዳለብን ራሳችን እናውቃለን፡፡
• ጠባቡ የኦነግ ህልም
ያለፈው የ50 ዓመት የነፃነት ትግል ተሞክሮ እንዳየነው በኢትዮጵያ ፀረ ህዝብ ይሁን ህዝባዊ መንግስት ቢቀያየሩም ነፃነታችን የማረጋገጥ ምኞታችን ኣያሳኩልንም፡፡ የተበታተነችና የተዳከመች ኢትዮጵያ እስካለች ድረስ ብቻ ነው የኦሮሞ ነፃ መንግስት መመስረት የሚቻለው፡፡ ስለዚ ኢትዮጵያን የመበታተን ዓላማ በመያዝ ከሰይጣንም ቢሆን አብረን መስራት አለብን፡፡
• የትምክህት ሃይሎች ህልም
ባለፉት መቶ አመታት እኛን የተፈታተነንና ያዳከመን ወያኔ በመሆኑ ወያኔን ለማዳከም ብሎም ለመደምሰስ ዓላማ ካነገቡ ሃይሎች አጥብቀን መስራት አለብን፡፡ ወያኔ በውስጥ ተቋዋሚ ሃይሎች ብቻ ሊደመሰስ አይችልም፡፡ እንኳን አሁን፣ ድሮም ዘመናዊ ትጥቅና ግማሽ ሚሊዮን ጠንካራ ሰራዊት ይዘንም አልቻልነውም ስለዚ እንደ ጌቶቻችን ከግብፅ ጋር ኣባይን ለድርድር በማቅረብ ወያኔን መደምሰስ አለብን፡፡ ወያኔ ከተደመሰሰ የነኦነግና የሌሎች አያያዝ ራሳችን እናውቅበታለን፡፡

  1. yaynshet Gebremedhn says

    በርግጥ በእምነት እንኳን ብናስብ ኢትዮጵያ እጇ ወደ ፈጣሪዋ ትዘረጋለች ነው የሚባለው ! በፖለቲካዊ ትንታኔ እና በሞራላዊ ትንታኔ ብናይም በኣሁኑ ግዜ የጥምረቱ ጥቅም የማይገባው ኢትዮጵያዊ በጣም ትንሽና ምናልባም በአስተዳደግ ወንድሙ ትቶ ለብቻው መብላት የለመደ ሰው የሚያራምደው ሃሳብ ነው ቢየ ነው የምደመድመው::
    ለዛም ወደ ሌላው ጫፍ ማለት ኤርትራና ጅቡቲ በኮንፈደሬሽን በማግባት ትልቋ ኢትዮጵያ እንዴት ንፍጠር የሚል ዜጋ የሚበዛው ነው የሚመስለኝ !! በአሁኑ ሳዓት ዜጋው የሰላም ጥቅም ገብቶታል ስለዚህ ለነዚህ ሃይሎች የሚምበረከክ ወጣትም አለ ቢየ አልስብም ቢኖርም እንኳን የተወናበደ ብቻ ነው ቢየ አስባለሁ ::

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy