የሀገሪቱን ሰላም የማይሹ ኃይሎች ከውጭ ጠላቶች ጋር በማበር በሀገሪቱ ህዝብ ሰላም፣ ፀጥታና ደህንነት ላይ የደቀኑትን ከፍተኛ ስጋት ለመቀልበስ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከትንናንት ጀምሮ የሚተገበር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አዋጀ።
የሀገሪቱን ሰላም የማይሹ ኃይሎች ከውጭ ጠላቶች ጋር በማበር በሀገሪቱ ህዝብ ሰላም፣ ፀጥታና ደህንነት ላይ የደቀኑትን ከፍተኛ ስጋት ለመቀልበስ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከትንናንት ጀምሮ የሚተገበር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አዋጀ።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሀገሪቱ እየደረሰ ባለው የህይወት መጥፋትና ከፍተኛ የንብረት መውደም ላይ በሰፊው ከመከረ በኃላ የአስኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጁን የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ለኢትዮጵያ ህዝብ ባስተላለፉት መልዕክት ገልፀዋል።
የአቸስኳይ ጊዜ አዋጁ በህገ መንግስቱ የተደነገጉ መሰረታዊ የሰብአዊ መብቶችንና በቬና ኮንቬንሽን ጥበቃ የሚደረግላቸው የድፕሎማቲክ መብቶች እንደማይጣሱም ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ አስታውቀዋል።
አላማውም ህዝብና መንግስት የጀመራቸውን የመፍትሄ ጥረቶች ማፋጠን መሆኑንም ነው የተናገሩት።
የአስኳይ ጊዜ አዋጁ እንደሁኔታው እየታየ ለ6 ወራት ያህል የሚዘልቅ መሆኑም ተመልክቷል።