Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኮማንድ ፖስቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማስፈፀሚያ መመሪያ ዝርዝር ይፋ አደረገ

0 429

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኮማንድ ፖስቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማስፈፀሚያ መመሪያ ዝርዝር ይፋ አደረገ
ጥቅምት 05፣ 2009


ኮማንድ ፖስቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማስፈፀሚያ መመሪያ ዝርዝር ይፋ አደረገ።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ትናንት ጥቅምት 4፣ 2009 ባካሄደው ስብሰባ ኮማንድ ፖስቱ አዋጁን ለማስፈፀም የሚያስችለውን መመሪያ እንዲያዘጋጅ የሚያመላክት ደንብ ማፀደቁን ተልከትሎ ነው የአዋጁ ማስፈፀሚያ መመሪያ ዛሬ ይፋ የሆነው ።
ኮማንድ ፖስቱ ዛሬ ይፋ ያደረገው መመሪያ በተለያዩ አካባቢዎች የሚወሰዱ እርምጃዎችን በዝርዝር ለይቶ ለህዝቡ ይፋ ማድረግ አለበት ለሚለው የደንቡ አካል መልስ የሚሰጥ ነው ።
የህዝብን ደህንነት እና ህገ መንግስታዊ ስርዓትን አደጋ በሚጥሉ የሁከት እና ነውጥ ተግባራት ተሳትፈው የተገኙ ግለሰቦች ላይ የሚወሰዱ እርምጃዎችንም መመሪያው አካቷል።
31 አንቀፅ ባሉት በዚሁ መመሪያ መሰረት ፣ሁከትና ብጥብጥ እንዲሁም በህዝቦች መካከል መቃቃሮችን የሚፈጥሩ ይፋዊም ሆነ ድብቅ ቅስቀሳዎች በማናቸውም መልኩና ዘዴ ተልክለዋል።
ከሽብተኛ ድርጅቶች ጋር የሚኖር መስተጋብርና በልሳኖቻቸውን መገልገል ላይም በተለይ እንደ ኢሳት፣ ኦ.ኤም.ኤን. እና መሰል የአሸባሪ ድርጅቶች ሚዲያዎች ላይ መመሪያው እገዳ ጥሏል።
ያልተፈቀደ ሰልፍና የአደባባይ ስብሰባ፣ ለህዝብ አገልግሎት አለመስጠት፣ በትምህርትና በስፖርት ማዘውተሪያ አድማ ማድረግ በክልከላው ተካተዋል።
ኮማንድ ፖስቱ ባወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማስፈፀሚያ መመሪያ በህዝባዊ ባዕላት ላይ ሁከትና ብጥብጥ ሊፈጥሩ የሚችሉ ቅስቀሳዎችን ማድረግና ማወክ ፣በመሰረት ልማቶች ላይ ጉዳት ማድረስ፣ሰላማዊ የትራፊክ እንቅስቃሴን ማወክ፣የህግ አስከባሪዎችን ስራ ማወክምን መመሪያው በፅኑ ይከለክላል።
ያልተፈቀደ አልባሳት መልበስ፣የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት፣ ህገ መንግስታዊ ስርዓትና የሀገር ሉዓለዊነትን የሚጎዳ ተግባር መፈፀም፣ያልተፈቀደ ቦታ መገኘት መምሪያው ካቀፋቸው ክልክላዎች ውስጥ ተካተዋል።
መቀመጫቸውን በኢዲስ አበባ ያደረጉ የውጭ አገራት ድፕሎማቶች ያለ ኮማንድ ፖስቱ እውቅና ውጭ ከአዲስ አባባ ከ40 ኪሎ ሜትር ራዲየስ ውጭ መንቀሳቀስ እንደማይችሉም ኮማንድ ፖስቱ አስታውቋል።
የህግ አስከባሪ አካላት ትጥቃቸውን ለሶስተኛ ወገን አሳልፈው መስጠትና ያለ አስገዳጅ ምክንያት ከስራ መልቀቅና ፈቃድ መጠየቅ እንደማይችሉም ተቀምጧል።
ኮማንድ ፖስቱ በተወሰኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች እየለየ ይፋ የሚያደርጋቸውን ክልክል ተግባራት ለይቶ አስቀምጧል።
እነዚህም የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ፣በልማት አውታሮችና በመሰረተ ልማቶች አቅራቢያ ከቀኑ 12 ሰዓት በኃላ እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት ድረስ ከተፈቀደለት ሰራተኛ በስተቀር መንቀሳቀስ የህግ አስከባሪዎች አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ ያስላቸዋል ይላል መመሪያው።
የሰዓት እላፊ በሚጣልበት ቦታና ጊዜ ክልከላን በመተላለፍ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ እንደማይቻልም ኮማንድ ፖስቱ አስታውቋል።
በተጨማሪም መመሪያው መረጃ የመስጠት የመተባበር ግዴታንም አስተቀምጧል።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ማስፈፀሚያ መመሪያ የደነገጋቸውን ክልክላዎች ተላልፎ በተገኘ ግለሰብ ላይ ይወሰዳሉ ያላቸውንም እርምጃዎች ይዘረዝራል።
እርምጃዎቹም ካለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ከሚደረግ ብርበራ አንስቶ በቁጥጥር ስርማዋልና የህግ አስከባሪዎች አስፈላጊውን አግባብነት ያላቸውን እርምጃዎች መውስድ የሚያችላቸውን ስልጣንንም ዘርዝሯል።
ኮማንድ ፖስቱ ተጠርጣሪዎችን ለፍርድ ቤት በማቅረብና በተሃድሶ የሚለቀቁትን እየለየ የእርምት እርምጃ በመውሰድ አዋጁ ፀንቶ እስከሚቆይበት ጊዜና ሰላምና መርጋጋት እስኪ መለስ ድረስ አገሪቱን በበላይነት እንደሚመራም በመግለጫው
ሰባት አባላት ያሉት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ኮማንድ ፖስት በጠቅላይ ሚንስር ኃይለማርያም ደሳለኝ የሚመራ ሲሆን የሀገሪቱ መከላከያ ሚንስትርምሴክሬታርያትሆኖ እንደሚያገለግል ከዚህ ቀደም በተሰጡት መግለጫዎች መገለፁ ይታወሳል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy