Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ለአስቸኳይ የጊዜ አዋጁ መመርያ ተፈፃሚነት የህዝቡ የነቃ ተሳትፎ ወሳኝነት አለው።

0 1,418

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ለአስቸኳይ የጊዜ አዋጁ መመርያ ተፈፃሚነት የህዝቡ የነቃ ተሳትፎ ወሳኝነት አለው። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ታውጆ ለህዝብ ይፋ ከተደረገበት ጊዜ አንስቶ በየጊዜው የተለያዩ መመርያዎች እየወጡና እየተፈፀሙ ሲሆን በርካታ ለውጦችም ታይተዋል። ሰላም ወዳዱ ህዝብ የፀረ ሰላም ሀይሉ ተልእኮ አንግበው የህብረተሰብ ሰላም በማወክ፣የህዝብና የመንግስትን ንብረት በማውደም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ሰላም ከማደፍረስ ባሻገር ከስራ በማፈናቀል ለተለያዩ ችግሮች የዳረጉ አካላትን መንግስት የፀጥታ አካላት ጋር በመሆን ለህግ እንዲቀርቡ ከማድረግ ረገድም ንቁ ተሳታፊ በመሆን ለአካባቢውና ለሀገሩ ሰላም ዘብ መቆሙን በተግባር በማስመስከር ላይ ይገኛል። የጥፋት ሀይሎቹ ለተሰማሩበት የጥፋት ተግባር ተሳታፊ እና ዋንኛ አቀንቃኝ የሆኑት ኑሮአቸውን በውጭ ሀገራት ባደረጉ የከሰሩ ፖለቲከኞች ተደልለው እና የነዚህ አካላት ተልእኮ ሀገር ማፈራረስ መሆኑን ካለመረዳት የመነጨ ሳይሆን ይህን እናደርግላችኃለን፣ይህን እንሰጣችሀለን በማለት አንድ ዝቅተኛ ገቢ ያለው ሰራተኛ የወር ደሞዝተኛ ወርሀዊ ደሞዝ ባነሰ ገንዘብ በመደለል ነው። እነዚህ የጥፋት ሀይሎች የጥፋት ተልእኮ አስፈፃሚዎች ባቃጠልዋቸው ፋብሪካዎች ይሁኑ ሌሎች ተቋማት ተቀጥረው የመስራት ፍላጎት እና ራስን የመቻል አላማ ቢኖራቸው ኖሮ የጥፋት ሀይሎቹ ለመደለያነት ከሚወረውሩላቸው የእለት ጉርስ እንኳን ከማትሸፍን ገንዘብ በተሻለ ከራሳቸው አልፈው ተጨማሪ ቤተሰቦቻቸውን ለማስተዳደር የሚችሉበት ገቢ ማግኘት እንደሚችሉ መረዳት ሳይችሉ ቀርተውም ሳይሆን በስራቸው ብዙ የህብረተሰብ ክፍሎች ሰርተው ቤተሰቦቻቸውን የሚያስተዳደሩበት ፋብሪካ ማቃጠል እና ሰራተኞችን ማፈናቀል ጀብድነት አልያም ጀግንነት ነው ብለው ከፈጠሩት ጨቅላ አስተሳሰብ የመነጨ ነው። የሚንስትሮች ምክርቤት የአስቸኳይ የጊዜ አዋጁ ይፋ ካደረገ ቡሀላ እና አዋጁን ለማስፈፀም ያቋቋመው ኮማንድ ፖስት ወደ ተግባር ገብቶ በየጊዜው የተለያዩ መመርያዎችን በማውጣት ለመመርያዎቹ ተግባራዊነት የአፈፃፀም አቅጣጫ በማስቀመጥ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶም ህብረተሰቡ በውስጡ የሚገኙትን የጥፋት ሴራ ተላላኪዎችን በማጋለጥ እና ከመሸጉበት በማውጣት ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት አሳልፎ በመስጠት እና የአስቸኳይ የጊዜ አዋጁ መመርያን በመከተል ራሳቸው የጥፋት ሀይሎች ጉዳይ አስፈፃሚዎች ከነትጥቃቸው ሳይቀር ለመንግስት የፀጥታ ሀይሎች እጃቸውን በመስጠት ላይ ይገኛሉ። ምንም እንኳን የአመፁ መነሻ ጥያቄ የመልካም አስተዳደር ችግር አለ በሚል ሽፋን የሚነሳና ህገመንግስቱን በአመፅ ለመናድ የሚንቀሳቀሱ ሀይሎች የጥፋት እንቅስቃሴያቸውን በማካሄድ እቅዳቸውን ለማሳካት ተጠቅመው ድብቅ አጀንዳቸውን ለማራመድ መጠቀማቸው ተገቢ ባይሆን የተለያዩ አካባቢዎች ከህዝቡ የሚነሱ ጥያቄዎች እንዴት መመለስ እንዳለበት ሊያስብበት ይገባል ።ከዚህ በተጨማሪ የተጣለባቸውን ሀላፊነት በመዘንጋት ህዝብ እንዲማረር መንስኤ የሆኑ የስራ ሀላፊዎች በፈፀሙት በደል በህግ እንዲጠየቁ መደረግ ስላለበት መንግስትጰጰ የጀመረው ውስጥን የማጥራት ዘመቻ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል። ህብረተሰቡም የአካባቢውን ብሎም የሀገሪቱን ሰላም ለመጠበቅ ፀረ ሰላም ሀይሎችን እና ፀረ ልማት ሀይሎች ተልእኮ አስፈፃሚዎችን በማጋለጥ ለአስቸኳይ የጊዜ አዋጁ ተፈፃሚነት ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ ይኖርበታል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy