Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የአፈፃፀም መመሪያ አንቀፅ 4 ለህዝብ አገልግሎት አለመስጠት የሚለውን ድንጋጌ በመተላለፍ

0 434

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የአፈፃፀም መመሪያ አንቀፅ 4 ለህዝብ አገልግሎት አለመስጠት የሚለውን ድንጋጌ በመተላለፍ
√ በጎንደር ከተማ የንግድ ሱቆቻቸውን በመዝጋት አገልግሎት ለማቋረጥ የተንቀሳቀሱ 13 የሚሆኑ ነጋዴዎች፣
√ የስራ ማቆም አድማ እንዲደረግ ውስጥ ውስጡን ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሌሎች 13 ተጠርጣሪዎች
√ እንዲሁም ከትምህርት ገበታ ሆነ ብለው በመቅረት የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማደናቀፍ የሞከሩ ሶስት አስተማሪዎች ህብረተሰቡ በሰጠው ጥቆማ በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ ይገኛል::

√ በባህር ዳር ከተማ የንግድ ሱቆቻቸውን በመዝጋት አገልግሎት ለማቋረጥ የተንቀሳቀሱ እና ህዝቡ በሰጠው ጥቆማ በቁጥጥር ስር ከዋሉት 35 ነጋዴዎች መካከል ስድስቱ ጉዳያቸው ተጣርቶ ሲለቀቁ የቀሩት 29 የንግድ ተቋማት ባለቤቶች ጉዳያቸው እየተጣራ ይገኛል::

ኮማንድ ፖስቱ ባለፈው አንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በአንዳንድ የአገሪቱ አከባቢዎች ተቀስቅሶ በነበረ ሁከት በቡድን ወይም በግል የተሳተፈ፣ የጦር መሳሪያ ወይም ማንኛውንም የግልም ሆነ የመንግስት ንብረት የዘረፈ፣ ለህገወጥ ተግባራት የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ ያደረገ፣ ወረቀት በመበተን አድማ በማድረግ የተሳተፈና ያነሳሳ እንዲሁም ሰው የገደለ፣ ማንኛውንም ንብረት ያቃጠለና ወንጀል የፈፀመ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የእርምጃ አፈፃፀም መመሪያ አንቀፅ 31 መሰረት የተሰጠውን የጊዜ ገደብ ከማለቁ በፊት በቀሩት አምስት (5) ቀናት ውስጥ በአቅራቢያው ለሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ እጁን እንዲሰጥና የዘረፈውን ንብረት እንዲያስረክብ አሳስቧል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy