በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የአፈፃፀም መመሪያ አንቀፅ 4 ለህዝብ አገልግሎት አለመስጠት የሚለውን ድንጋጌ በመተላለፍ √ በጎንደር ከተማ የንግድ ሱቆቻቸውን በመዝጋት አገልግሎት ለማቋረጥ የተንቀሳቀሱ 13 የሚሆኑ ነጋዴዎች፣ √ የስራ ማቆም አድማ እንዲደረግ ውስጥ ውስጡን ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሌሎች 13 ተጠርጣሪዎች √ እንዲሁም ከትምህርት ገበታ ሆነ ብለው በመቅረት የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማደናቀፍ የሞከሩ ሶስት አስተማሪዎች ህብረተሰቡ በሰጠው ጥቆማ በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ ይገኛል::