Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኢሬቻ የኦሮሞ የማንነት መገለጫ በዓል!!

0 1,131

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኢሬቻ የኦሮሞ የማንነት መገለጫ በዓል!!

ኢሬቻ በመሰረቱ የኦሮሞ ህዝብ የዋቄፈና ሃይማኖት ተከታዮች ለፈጣሪያቸው (ለዋቃ) ምስጋና የሚያቀርቡበት ስርዓት ነው፡፡

የዋቄፈና እምነት ተከታዮች ኢሬቻ/ኢሬሳ ማለትም እርጥብ ሳር በመያዝና ሆራ ላይ በማስቀመጥ /waaqa dukkana gannaatii booqaa birraatti nu baafte, waaqa tulluu uumte waaqa malkaa uumte galanni siif haa ta’u/ ማለትም ከጨለማው የክረምት ዘመን ወደ ብርሃን ወቅት ያሸጋገርከን፣ ወንዞችን፣ ተራሮችን የፈጠርክ አምላክ ምስጋና ይገባሃል በማለት ለአምላካቸው ምስጋና ያቀርባሉ፡፡ ዋቄፈና/ waaqeffannaa/ እምነቱ ነው፤ ዋቄፈታ/waaqeffataa/ የወንድ አማኝ ሲሆን ዋቄፈቱ/waaqeffattuu/ ደግሞ የሴት አማኝ ናት፡፡

የዋቄፈና እምነት አገር በቀል የኦሮሞ ህዝብ እምነት ነው፤ የኦሮሞ ህዝብ ከጥንት ጀምሮ በተመረጡ ሆራዎች ላይ ጸሎቱን ሲያደርስ ቆይቷል፡፡ ከተመረጡት የኢሬቻ ቦታዎች ዋነኛው በቢሾፍቱ የሚገኘው ሆራ አርሰዲ ነው፡፡ ህዝቡ በየዓመቱ መስከረም መጨረሻ አከባቢ በአንድነት በሆረ አርሰዲና በሌሎች በተመረጡ ሆራዎች ወይም መልካዎች በመሰባሰብ በዓሉን ያከብራል፡፡

በበዓሉ ላይ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የዋቄፈና እምነት ተከታዮችና ሌሎች በተለያዩ በኦሮሞ ባህላዊ አለባበሶች ተውበውና እርጥብ ሳር/ ireecha/irreessa/ በመያዝ በዓሉን ያከብራሉ፡፡
ኢሬቻ በዓመት ውስጥ ሁለት ጊዜ የሚከበር ሲሆን አንዱ በተራራዎች ላይ የሚከበር/ Irreecha tulluu/ ሲሆን ሌለው ደግሞ በሃይቆች ወይም ወንዞች ላይ የሚከበር /Irreecha malkaa/ ይባላሉ፡፡

በዝግጅቱ ላይ የኦሮሞ አባገዳዎች ለማህበረሰቡ መልዕክት ያስተላልፋሉ፤ የተለያዩ ባህላዊ ጭፈራዎችና ሌሎች በህላዊ ክንውኖች ይደረጋሉ፡፡

ዘንድሮም የገዳ ስርዓት አካል የሆነው የኢሬቻ በዓል የፊታችን መስከረም 22 በኦሮሚያ ክልል ደረጃ በቢሾፍቱ ከተማ በሆራ አርሰዲ ይከበራል፡፡

በቀጣይም በዓሉን ተከትሎ የኦሮሞ የገዳ ስርዓት በማይዳሰስ ቅርጽነት በመንግስታቱ ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስ፣ እና የባህል ድርጅት (UNESCO) ለማስመዝገብ ጥረቶች እየተደረጉ ነው፡፡

የኦሮሞ ህዝብ ከጥንት ጀምሮ ዴሞክራሲያዊና አገር በቀል በሆነው ገዳ ስርዓት ሲተዳደር ነበር፣ የራሱ የሆነ አገር በቀል እምነት ዋቄፈና እና የእምነቱ የምስጋና ማቅረቢያ ቦታ ኢሬቻ የነበረው ህዝብ ነው፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy