NEWS

ኢትዮጵያን የማዳከምና የመበታተን ዓላማ ያነገቡ ሃይሎች ቅዠት

By Admin

October 26, 2016

ኢትዮጵያን የማዳከምና የመበታተን ዓላማ ያነገቡ ሃይሎች ቅዠት • የግብፅ አክራሪ ሃይሎች ህልም ያለፉት በ100ዎች የሚቆጠሩ ዓመታት ተሞክሮ እንደሚነግረን የደኸየችና የተዳከመች ኢትዮጵያ እስካለች ድረስ ብቻ ነው የናይል ውሃ እንደፈለግን የምንጠቀምበት፣ ትርፍ ውሃ ካለም ለአረብ አገራትና ለእስራኤል በመሸጥም ገቢ ልናገኝበት የምንችለው፡፡ ጠንካራና የበለፀገች ኢትዮጵያ ካለች ግን ይህ ጥቅም ሳንወድ ትጋራናለች፡፡ ስለዚ የደኸየችና የተዳከመች ኢትዮጵያ እንድትሆን ጠንክረን መስራት አለብን • የሻዕብያ ስርዓት ህልም የ25 ዓመት ተሞክሮ እንደሚያሳየው የደኸየችና የተዳከመች ኢትዮጵያ እስካለች ድረስ ብቻ ነው በኢትዮጵያ ውስጥ ገብተን የኢትዮጵያ ሃብት እንደፈለግን እናተራምሳለን፡፡ ጠንካራና የበለፀገች ኢትዮጵያ ካለች ግን ይህ ጥቅም ይቀርብናል፡፡ ስለዚ የደኸየችና የተዳከመች ኢትዮጵያ እንድትኖር አንድነትም ነፃነትም ከሚመኙ ሃይሎች ጠንክረን መስራት አለብን፡፡ በመጨረሻም ምን ማድረግ እንዳለብን ራሳችን እናውቃለን፡፡ • ጠባቡ የኦነግ ህልም ያለፈው የ50 ዓመት የነፃነት ትግል ተሞክሮ እንዳየነው በኢትዮጵያ ፀረ ህዝብ ይሁን ህዝባዊ መንግስት ቢቀያየሩም ነፃነታችን የማረጋገጥ ምኞታችን ኣያሳኩልንም፡፡ የተበታተነችና የተዳከመች ኢትዮጵያ እስካለች ድረስ ብቻ ነው የኦሮሞ ነፃ መንግስት መመስረት የሚቻለው፡፡ ስለዚ ኢትዮጵያን የመበታተን ዓላማ በመያዝ ከሰይጣንም ቢሆን አብረን መስራት አለብን፡፡ • የትምክህት ሃይሎች ህልም ባለፉት መቶ አመታት እኛን የተፈታተነንና ያዳከመን ወያኔ በመሆኑ ወያኔን ለማዳከም ብሎም ለመደምሰስ ዓላማ ካነገቡ ሃይሎች አጥብቀን መስራት አለብን፡፡ ወያኔ በውስጥ ተቋዋሚ ሃይሎች ብቻ ሊደመሰስ አይችልም፡፡ እንኳን አሁን፣ ድሮም ዘመናዊ ትጥቅና ግማሽ ሚሊዮን ጠንካራ ሰራዊት ይዘንም አልቻልነውም ስለዚ እንደ ጌቶቻችን ከግብፅ ጋር ኣባይን ለድርድር በማቅረብ ወያኔን መደምሰስ አለብን፡፡ ወያኔ ከተደመሰሰ የነኦነግና የሌሎች አያያዝ ራሳችን እናውቅበታለን፡፡