Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የኢህአዴግ በጥልቀት የመታደስ ሂደት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሷል

0 416

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የኢህአዴግ በጥልቀት የመታደስ ሂደት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሷል

ጥቅምት 21፣2009

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር /ኢህአዴግ/ ያለፉትን 15 ዓመታት ጉዞውን በመገምገም የጥልቅ ተሃድሶ ሂደቱ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሷል።

በተለይ ስልጣንን ለህዝብ አገልግሎት ማዋል የሚለው በተሃድሶው ሂደት አብይ መርህ ሆኖ  ቀርቧል፡፡

የኢትዮጵያ  ህዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር /ኢህአዴግ/ ያለፉትን 15 አመታት የተሃድሶ ጉዞ ገምግሞ ዳግም በጥልቅ  መታደስ  ማድረግ እንደሚገባው  መግለጹ ይታወሳል። የሚነሱ የህዝብ ጥያቄዎችን በአግባቡ የሚመልስ አደረጃጀትም እንደሚፈጥር አስታውቋል።

ድርጅቶቹ በጥልቅ መታደስ የሚለውን ንቅናቄ መሰረት በማድረግ  ውስጣቸውን በሚገባ መፈተሻቸውን የኢህአዴግ መስራች ድርጅቶች በግምገማቸው ዙሪያ በሰጡት አስተያየት ገልፀዋል።

መስራች ድርጅቶቹ  የአሁኑ ተሃድሶ የህዝቡን ተጠቃሚነት እና ፍላጎት ለማሟላት የሚጎዱ ድክመቶችና ስህተቶችን በማረም ህዝብን የመካስ ተሃዲሶ እንደሆነ ተነግረዋል።  ሙስናና ብልሹ አሰራሮችም በድርጅቱ ውስጥ እንዳይታይ ጠራርገው ማስወጣት እንዳለባቸውም አክለው ገልፀዋል።

እነዚህ መሰረታዊ ጉዳዮችም በአንዴ የሚመጡ ሳይሆኑ በሂደት የሚረጋገጡ ናቸው ያሉት የመስራች ድርጅቶች፣ አመራሮች ለዚህም ህዝባዊ ተሳትፎ ወሳኛ እንደሆነ ተናገረዋል።

ስልጣንን  ለህዝብ ጥቅም ለማዋል ቁርጠኝነት አሳያለሁ ባለው አመራር ውስጥ ክፍተት ቢገኝ ለማረቅ ተገቢውን ዝግጅት ማድረጉንም አስፈፃሚውን የመቆጣጠር ስልጣን ያለው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ገልጿል።

ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ የመንግስትን የአመቱን የስራ አቅጣጫ ለመጠቆምና ለሁለቱ ምክር ቤቶች ባደረጉት ንግግርም በአመቱ በተለያዩ አከባቢዎች የታዩ ተቃውሞዎችን በአግባቡ ለመመለስ ለወጣቶች የሚሰጥ ትኩረት ቀዳሚ እንደሚሆን ተናግረዋል።

የፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ንግግር ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ ለመስጠት ወደ ምክር ቤቱ የሚመጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃ/ማሪያም ደሳለኝ የብዙዎችን ጥያቄ ይፈታሉ የተባሉ እቅዶችን  ለመተግበር የመንግስትን ቁርጠኝነትና የሚከተሉትን መንገድ በነገው እለት ለፓርላማው ይፋ ያደርጋሉ። አዲሱን የፌዴራል መንግስት ካቢኔም ይፋ ያደርጋሉ  ተብሎ  ይጠበቃል።

በዚህ ጉዳይ ላይ ብሩክ ያሬድ ያጠናቀረው ዘግባ እንደሚከተለው ቀርቧል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy