CURRENT

የኢሬቻ ዋዜማ በቢሾፍቱ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበረ

By Admin

October 01, 2016

የኢሬቻ ዋዜማ በቢሾፍቱ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበረ

እሁድ መስከረም 22 በደማቅ ሁኔታ ለሚከበረው የኢሬቻ በአልን ለማስተናገድ የቢሾፍቱ ከተማ ዝግጅቷን አጠናቃለች፡፡ በአሉን ለማክበር ከተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የመጡ እንግዶች ወደ ከተማዋ መግባት ጀምረዋል፡፡ በቢሾፍቱ ከተማ በተለያዩ በኦሮሞ ባህላዊ አልባሳት ያሸበረቁ ታዳሚዎች የጎዳና ላይ ትርኢቶችን ታድመዋል፡፡ የጎዳና ላይ ትርኢቶቹ ታላቁ የኢሬቻ ሩጫ፣ የፈረስ ግልቢያ፣ የማርሽ ባንድ ትርኢቶችና የመሳሰሉት ነበሩ፡፡