Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ግብፅ ለምን የተሳሳተ መንገድ መረጠች?

1 754

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ግብፅ ለምን የተሳሳተ መንገድ መረጠች?

ታላቁ የህዳሴ ግድብ ለታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው በጥናት አረጋግጣ ወደ ግንባታ የገባችው ኢትዮጵያ የግድቡን ግንባታ አጋምሳለች። ሀገሪቱ የታችኛው ተፋሰስ ሀገራትን ጥርጣሬ ለመፋቅ አለም አቀፍ ባለሙያዎች በግድቡ ላይ ጥናት አካሂደው ምክረ ሀሳብ እንዲለግሱ እስከ ማድረግ ዘልቃለች። የጥናት ቡድኑ ሪፖርትም ግድቡ በታችኛቸው ተፋሰስ ሀገሮች ላይ ይህ ነው የሚባል ጉዳት እንደማያስከትል አረጋግጧል፡፡ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በጉዳዩ ላይ ያነጋገራቸው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የምህንድስና መምህሩ ዶክተር መሰለ ሃይ፣ ከሃይድሮ ፓወር ሳይንስ አንፃር ሲታይ ታላቁ የህዳሴ ግድብ እና የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት እንደሚጠቅም ጥርጥር የለውም ይላሉ።

ሱዳን የአባይ ውሃን ተጠቅማ መረዌ ከሚባል ግድብ የኤሌክትሪክ ሃይል ታገኛለች። ግብፅ መስኖዋን አጠጥታ፤ የዜጎቿን ጉረሮ አርሳ፤ በአባይ ውሃ ከአስዋን ግድብ የኤሌክትሪክ ሀይል ታገኛለች። የአባይ ውሃ በክረምት ወቅት ይህንን ሁሉ ተግባር ከውኖ የተረፈው የሜዲትራንያን ባህርን ይቀላቀላል። አስዋን በብዙ ቢሊየን ኪዩቢክ ሊትር የሚለካ ውሃን በትነት ያጣል፡፡ የአባይ ውሃ ከኢትዮጵያ ጠራርጎ በሚወስደው አፈር የአስዋን እና የመረዌ ግድብን በደለል ሞልቶ ከተሞቻቸውን በጎርፍ ያጥለቀልቃል። እናም ታለቁ የህዳሴ ግድብ ሀገራቱን ከዚህ ችግር የሚታደግ መሆኑን ነው ምሁሩ የተናገሩት።

በአጠቃላይ ግድቡ ተቆጥሮ የማያልቅ ጥቅምን ለሶስቱም ሀገራት እንደሚሰጥ በሳይንስ የተረጋገጠ ሃቅ ነው። ሶስቱ ሀገራትም ይህንን እውነት ያጡታል ተብሎ አይጠበቅም፡፡ በታላቁ የህዳሴ ግደብ ላይ በትንሹ ሊነሳ የሚችለው ጉዳይ የውሃ መሙያ ጊዜው ነው፡፡ ዶክተር መሰለ ይህም በሳይንስ ደረጃ ከታየ በቀላሉ በድርድር ሊፈታ የሚችል ጉዳይ ነው የሚል ሃሳብ ያነሳሉ። እናም ከሃይድሮ ፓወር አንፃር ታላቁ የህዳሴ ግድብ የታችኛው ተፋሰስ ሀገራትን ለትብብር የሚጋብዝ የጋራ ፕሮጀክት መሆን ነበረበት። ሁለቱ የታችኛው ተፋሰስ ሀገራትም ኢትዮጵያ በግዙፍ ፕሮጀክቷ እየመጣች ላለው ትሩፋት ብድራትን በከፈሏትም ነበር ይላሉ ምሁሩ።

ሱዳን ግድቡ እንደሚጠቅማት አረጋግጣ የግድቡን ግንባታ እንደምትደግፍ ይፋ ካደረገች አመታት ተቆጥረዋል። ግብፅ ግን የግድቡን ግንባታ ከመደገፍ ይልቅ በተቃራኒው መቆምን መርጣለች፡፡ አሁንም ብዙ የስምምነት መንገዶችን አሳብራ ከመጣች በኋላ ለረጅም አመታት ውስጥ ለውስጥ ስትጎነጉን የነበረውን የግድቡን ግንባታ የማስተጓጎል ሀሳብ የሚያጋልጡ ተግባራትን እየፈፀመች ትገኛለች። የግድቡ መገንባት ጥቅም እንጂ ጉዳት እንደማያመጣባት እየታወቀ ግብፅ ለምን ይህን የተሳሳተ መንገድን መረጠች?

ታላቁ መሪ መለስ ዜናዊ ይህን በተመለከተ እንዲህ ብለው ነበር፡፡ “ሀይድሮ ፓወር ላይ የሚያጣላ ነገር የለም፡፡ ምክንያቱም ውሃ አይያዝም፡፡ ነገር ግን የግብፅ ሀሳብ ኢትዮጵያ ስታድግ ኋላ ላይ ጥያቄ {ሌላ} ታነሳለች፤ ስለዚህ እዚያው ላይ እንያዛት፤ ሌላ ነገር ለማሰብ ጊዜ እንከልክላት የሚል ነው” ብለዋል።

  1. Mekonnen shalamo says

    እንጨሪሳለን በአገራችን መብታችን ነው.

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy