Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል ከአንድ ሺህ ሄክታር በላይ የሚገኘውን የእጣን ከርቤና ሙጫ ምርት ጥናትን መሰረት ባደረገ መልኩ ለማልማት ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰራ የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ::

0 2,631

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል ከአንድ ሺህ ሄክታር በላይ የሚገኘውን የእጣን ከርቤና ሙጫ ምርት ጥናትን መሰረት ባደረገ
መልኩ ለማልማት ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰራ የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ::
በቢሮው የተ ፈጥሮ ሀብት ልማት መምሪያ ሓላፊ አቶ ከደር አረብ ዛሬ እንደተናገሩት በክልሉ ዘጠኝ ዞኖች የሚገኘው
የእጣን ሙጫና ከርቤ ሀብት ስፋት መጠንና ለመለየት የሚያስችሉ ስራዎች ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በቅርበት
ለመስራት እቅድ መያዛቸውን ገልጸል::
በክልሉ በአመት ከሁለት ሺህ በላይ ኩንታል ማምረት እንደሚቻልም ሃላፊው ተናግረዋል ::
በቆረሓይ ዞን ቀብሪደሀር ወረዳ ጠላት ቀበሌ ነዋሪ አቶ አብዲላሂ መሁመድ በሰጡት አስተያየት ዛፍ ምርቱን
ያለምንም ገደብ በማሰባሰብ ለነጋዴዎች በተመጣጣኝ ዋጋ በማስረከብ ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልፀዋል::
“በአከባቢያችን ሙጫ ከርቤና እጣን ዛፍ በብዛት ይገኛል:: ተፈጥሮ ሀብቱን በማሰባሰብ ለነጋዴ በማቅረብ ተጠቃሚ
መሆን ችያለሁ”:: ምርቱ በብዛት ለማሰባሰብ እንዲንችል የሚመለከታቸው አካላት የብድር አቅርቦትና የቴክኒክ ድጋፍ
እንዲመቻችላቸው ጠይቀዋል::
አቶ ሙሴ ሀሰን ተባሉት ሌላው ቀበሌው ነዋሪ አርብቶ አደር 20 ኪሎ ግራም የሙጫ ምርትን በማሰባሰብ ሰባት ሺህ
ብር ገቢ ማገኘቱን ገለፀዋል::
“አልሀምዲ ሌላህ አከባቢያችን በተፈጥሮ የታደለ ነው እኔም ደስተኛ ነኝ ከምርቱ ከማገኘው ገቢ የራስንና ቤተሰብን
ወጪ እሸፍናለሁ”::
አቶ መሀድ አሊ የአለኣሚን ህብረት ስራ ማህበሩ ሊቀመንበር በበኩላቸው ማህበሩ የእጣን ከርቤና ሙጫ ምርትን
በመረከብ ለአገር ውስጥ ገቢ ያቀርባል::
በዚህም የተነሳ ገበያ እጥረት አለመኖሩን ተገለጹት አቶ መሀድ ዘርፉ ለሀገር እድገት የሚኖረው አስተዋፅኦ
ለማሳድግ የገበያ ትስስር እንዲፈጠሪላቸው ጠይቀዋል::
በዞኑ ሽኮሽ ወረዳ ነዋሪ ወይዘሮ ኢፍራህ አህመድ በሰጡት አስተያየት የአከባቢው ህብረተሰብ የእጣን እና ሙጫ
ምርትን ለባህላዊ ህክምናና ለሌሎች አገልግሎት እየተጠቀመ ይገኛል::
በሽኮሽ ከተማ እጣን ሙጫና ከርቤ ምርት ተረካቢ አቶ አህመድ አብዱላሂ እንዳሉት ምርቱን የሚሰባሰቡ አርብቶ
አደሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ ማምጣቱን ገልፀዋል::
ከተፈጥሮ ዛፍ የሚገኘው ከርቤ፣ሙጫና እጣን ምርት ለምግብነት ለመድሃኒት ምርት ግብኣትነት እንደሚዉል የተለያዩ
ጥናቶች ይጠቁማል::

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy