Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ብአዴን እያካሄደ ያለው ጥልቅ የተሀድሶ ግምገማ የሕዝቡን ጥያቄዎች ለመመለስ አቅም የሚፈጥር መሆኑ ተገለጸ

0 467

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ብአዴን እያካሄደ ያለው ጥልቅ የተሀድሶ ግምገማ የሕዝቡን ጥያቄዎች ለመመለስ አቅም የሚፈጥር መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 4፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ብአዴን እያካሄደ የሚገኘው በጥልቀት የመታደስ ግምገማ የድርጅቱን ውስጣዊ ችግሮች በመፍታት የሕዝቡን ጥያቄ በተሻለ ለመመለስ አቅም እንደሚሆን የድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

“በጥልቀት በመታደስ ክልላዊና ሀገራዊ ሕዳሴን እናሳካ” በሚል መሪ ቃል በብአዴን ከፍተኛና መካከለኛ አመራሩ እየተካሄደ ያለው የተሀድሶ ግምገማ እንደቀጠለ ነው።

የፅህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ አለምነው መኮንን እንዳሉት ብአዴን በሕዝብ ተወልዶ በሕዝብ ድጋፍ ያደገ ድርጅት ነው።

በብዝሃነት የተገነባውን ዴሞክራሲያዊ አንድነቱን እንደጠበቀ፣ ህዝባዊ ወገንተኝነቱንና የዓላማ ፅናቱን እንደተላበሰ ባለፉት ዓመታት ድሎችን ሲያስመዘግብ የቆየ ድርጅት መሆኑንም ገልፀዋል።

ድርጅቱ በተለያዩ ጊዜያት የገጠሙትን ፈተናዎች በሰከነ አካሄድ በመገምገምና ራሱን በራሱ በማስተካከል በክልሉም ሆነ በሀገሪቱ ለተመዘገበው ሁለንተናዊ እድገት የጎላ ሚና ማበርከቱንም አቶ አለምነው አስረድተዋል።

ይሁንና ባለፉት ጥቂት ጊዜያት በአመራሩ የቁርጠኝነት ማነስ፣ ስልጣንን ለግል ጥቅም ማዋል፣ የሥራ እጥነት ችግር፣ ሙስናና የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር እየገነነ መምጣቱ በሕዝብ ላይ ቅሬታ እየፈጠረ መምጣቱን ተናግረዋል።

የጥፍት ኃይሎችም የሕዝቡን ጥያቄ መነሻ በማድረግ በቀሰቀሱት ሁከትና ብጥብጥ የሰው ሕይወት መጥፋቱንና በብዙ ልፋትና ድካም በክልሉ ወደኢንቨስትመንት ሥራ የገቡ ተቋማት መውደማቸውን ገልጸዋል።

በተጨማሪም በሌሎች የግልና የመንግስት ንብረቶች ላይ ጉዳት መድረሱን ነው የገለጹት።

በሕዝቡ ላይ የተፈጠረውን ቁጣና ተቃውሞ ለማስተካከል ድርጅቱ ራሱን ማየት አስፈላጊና ወሳኝ ሆኖ መገኘቱን ተናግረዋል።

“በዚህም አመራሩ በጥልቀት ተገምግሞ ማስተካከያ ለማድረግ ርብርብ በመደረግ ላይ ነው” ብለዋል።

በተሀድሶ ግምገማው ለችግሮቹ መፈጠርና በወቅቱ መፍትሄ አለመስጠት አመራሩ ራሱን ተጠያቂ ያደረገ ሲሆን በመድረኩ ላይ የችግሩ መንስኤ ከነመፍትሄው እየተቀመጠ መሆኑን አብራርተዋል።

ከግምገማው በኋላ ድርጅቱን መልሶ ለማደራጀት ሰዎችን የመለየት ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ አቶ አለምነው አመልክተዋል።

በአሁኑ ወቅት በ14 መድረኮች ከ7 ሺህ በላይ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች የተሳተፉበት የጥልቅ ተሃድሶ ግምገማ በመካሄድ ላይ መሆኑን ገልጸዋል።

በቀጣይም ግምገማውን እስከታች ድረስ በማውረድ ከ1 ነጥብ 6 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ የድርጅቱ አባሎች ውይይት እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል።

ሕብረተሰቡና የመንግስት ሠራተኛውም ውይይት እንደሚደረግ ነው የጠቆሙት።

ጥልቅ የተሀድሶ ግምገማው ድርጅቱ ያሉበትን ችግሮች በመፈተሽና በማስተካከል የገጠመውን ፈተና በብቃት ለመወጣት አቅም ይፈጥርለታል ያሉት ሀላፊው፥ ብአዴን መስመሩን በማጥራት የሕዝብ ጥቅም ለማስከበር የሚያደርገው ትግል ለፍሬ እንዲበቃ ሕዝቡ የበኩሉን ሚና ሊወጣ እንደሚገባም አሳስበዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy