Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ በጅቡቲ ይፋዊ ጉብኝት አደረጉ

0 743

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ በጅቡቲ ይፋዊ ጉብኝት አደረጉ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ በጅቡቲ ይፋዊ ጉብኝት አደረጉ

የኢፌዲሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ በጅቡቲ ይፋዊ ጉብኝት አደረጉ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በጂቡቲ ቆይታቸው ከፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌ ጋር ተገናኝተው በሁለቱ ሀገራት መካከል ባለው የሁለትዮሽ ግንኙነት መጠናከር ዙሪያ ተወያይተዋል።

ዶክተር ወርቅነህ በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች ተከስቶ የነበረው የሰላም መደፍረስና አለመረጋጋት መቀልበሱንና ወደ ሰላማዊ ሁኔታ መመለሱን ለፕሬዝዳንቱ አብራርተዋል።

የኢትዮ ጂቡቲ ጠንካራ የሁለትዮሽ ኢኮኖሚያዊ፣ ፓለቲካዊና ማህበራዊ ግንኙነት የበለጠ እንዲጎለብት ለማድረግ የተቻላቸውን ሁሉ ጥረት አንደሚያደርጉም ገልፀውላቸዋል።

ፕሬዚዳንት ኦማር ጌሌ በበኩላቸው ቀጣዩ ጊዜ መልካም የስራ ጊዜ እንዲሆንላቸው መልካም ምኞታቸውን በመግለጽ የሁለትዮሽ ግንኙነቱ የበለጠ እንዲጠናከር በጋር መስራት ይኖርብናል ብለዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ በጉብኝታቸው ከጅቡቲ ውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ሙሀመድ አሊ የሱፍ ጋር ተገናኝተው በሁለቱ አገሮች ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ዙሪያ መክረዋል።

በተለይም የሁለቱን አገሮች የኢኮኖሚ ውህደት ማፋጠን በሚቻልበት ሁኔታ እንዲሁም በአካባቢያዊ አህጉራዊና አለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፋ ያለ ውይይት አካሂደዋል።

ዶክተር ወርቅነህ ከጀቡቲ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሁም ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ጋር ተገናኝተው በተለያዩ አገራዊና አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸውንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy