ምክር ቤቱ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ያቀረቡትን ካቢኔ አፀደቀ
አዲስ ተሿሚዎቹ የህዝብ አደራ በቁርጠኝነት መንፈስ ተግባራዊ ለማድረግ መዘጋጀታቸውን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።
አዲስ የተሾሙትን የካቢኔ አባላት ለምክር ቤቱ ያቀረቡት የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ሹመቱ የህዝቡን ጥያቄ በአግባቡ ለመመለስ ያለመ ነው ብለዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ የግለሰቦቹ የአመራር ብቃትና ፍላጎት፣ ህዝባዊ ወገንተኝነት፣ የትምህርት ዝግጅትና አግባብነት የአመራር ልምድ ተመዝኖ መሾማቸውን ተናግረዋል።
ምክር ቤቱ ካቢኔውን ሲያዋቅር በነባርነት የሚቀጥሉት 10 የቢሮ ሀላፊዎች
1. አቶ ብናልፍ አንዷለም – ምክትል ርዕሰ መስተዳደር
2. አቶ ተስፋየ ጌታቸው – የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ሀላፊ
3. ዶክተር ተሸመ ዋለ – ግብርና ቢሮ ሃላፊ
4. ወይዘሮ ገነት ገ/ እግዚአብሄር – ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሀላፊ
5. አቶ ጃንጥራር አባይ – የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ሀላፊ
6. አቶ ፍርዴ ቸሩ – የፍትህ ቢሮ ሀላፊ
7. ወይዘሮ ፈንታየ ጥበቡ – የሴቶችና ህጻናት ቢሮ ሀላፊ
8. አቶ ገለታ ስዩም – ሲቪል ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ ሀላፊ
9. አቶ ንጉሱ ጥላሁን – ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር
10. አቶ በድሉ ድንገቱ – ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር
አዲስ የተሾሙ ካቢኔዎች
1. ዶክተር ይልቃል ከፍ አለ አስረስ – የትምህርት ቢሮ ሀላፊ
2. ዶክተር አበባው ገበየሁ – የጤና ቢሮ ሀላፊ
3. አቶ ሞላ ፈጠነ – የውሃ መስኖ ኢነርጂ ቢሮ ሀላፊ
4. አቶ ጸጋ አራጌ – የመሬት አስተዳደርና ጥበቃና ቢሮ ሀላፊ
5. አቶ ፍስሃ ወልደሰንበት – የአስተዳደርና ጸጥታ ቢሮ ሀላፊ
6. ዶክተር ጥላሁን መሀሪ – የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ
7. ዶክተር ሂሩት ካሳው – የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ
8. አቶ ሞላ ጀንበሩ – የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ
9. አቶ መሀመድ አብዱ – የገቢዎች ባለስልጣን ዳይሬክተር
10. ዶክተር በላይነህ አየለ – የአካባቢ ደንና ዱር እንስሳት ቢሮ ሀላፊ
11. አቶ ላቀ አያሌው – የቴክኒክ ሙያና ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ሀላፊ
12. ወይዘሮ ወለላ መብራት – የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ
ምክር ቤቱ የቀረቡትን የካቢኔ አባላት ሹመት በአንድ ድምፀ ተአቅቦ በአብላጭ ድምጽ አፅድቋል።
አዳዲስ የተመደቡትና ነበራቹም በጥልቀት መታደስ ሂደቱ በግልጽ ታይተው የመጡና የክልሉን ህዝብ ጥያቄ ባጭር ጊዜ በመፍታት ልማቱን ለማስቀጠል የላቀ እምነት የተጣለባቸው ናቸው።
ተሿሚዎቹ በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ቃለ መሃላ ፈፀመዋል፡፡
በደመቀ ጌታቸው