English

በኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል ከአንድ ሺህ ሄክታር በላይ የሚገኘውን የእጣን ከርቤና ሙጫ ምርት ጥናትን መሰረት ባደረገ መልኩ ለማልማት ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰራ የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ::

By Admin

November 11, 2016

በኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል ከአንድ ሺህ ሄክታር በላይ የሚገኘውን የእጣን ከርቤና ሙጫ ምርት ጥናትን መሰረት ባደረገ መልኩ ለማልማት ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰራ የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ:: በቢሮው የተ ፈጥሮ ሀብት ልማት መምሪያ ሓላፊ አቶ ከደር አረብ ዛሬ እንደተናገሩት በክልሉ ዘጠኝ ዞኖች የሚገኘው የእጣን ሙጫና ከርቤ ሀብት ስፋት መጠንና ለመለየት የሚያስችሉ ስራዎች ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በቅርበት ለመስራት እቅድ መያዛቸውን ገልጸል:: በክልሉ በአመት ከሁለት ሺህ በላይ ኩንታል ማምረት እንደሚቻልም ሃላፊው ተናግረዋል :: በቆረሓይ ዞን ቀብሪደሀር ወረዳ ጠላት ቀበሌ ነዋሪ አቶ አብዲላሂ መሁመድ በሰጡት አስተያየት ዛፍ ምርቱን ያለምንም ገደብ በማሰባሰብ ለነጋዴዎች በተመጣጣኝ ዋጋ በማስረከብ ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልፀዋል:: “በአከባቢያችን ሙጫ ከርቤና እጣን ዛፍ በብዛት ይገኛል:: ተፈጥሮ ሀብቱን በማሰባሰብ ለነጋዴ በማቅረብ ተጠቃሚ መሆን ችያለሁ”:: ምርቱ በብዛት ለማሰባሰብ እንዲንችል የሚመለከታቸው አካላት የብድር አቅርቦትና የቴክኒክ ድጋፍ እንዲመቻችላቸው ጠይቀዋል:: አቶ ሙሴ ሀሰን ተባሉት ሌላው ቀበሌው ነዋሪ አርብቶ አደር 20 ኪሎ ግራም የሙጫ ምርትን በማሰባሰብ ሰባት ሺህ ብር ገቢ ማገኘቱን ገለፀዋል:: “አልሀምዲ ሌላህ አከባቢያችን በተፈጥሮ የታደለ ነው እኔም ደስተኛ ነኝ ከምርቱ ከማገኘው ገቢ የራስንና ቤተሰብን ወጪ እሸፍናለሁ”:: አቶ መሀድ አሊ የአለኣሚን ህብረት ስራ ማህበሩ ሊቀመንበር በበኩላቸው ማህበሩ የእጣን ከርቤና ሙጫ ምርትን በመረከብ ለአገር ውስጥ ገቢ ያቀርባል:: በዚህም የተነሳ ገበያ እጥረት አለመኖሩን ተገለጹት አቶ መሀድ ዘርፉ ለሀገር እድገት የሚኖረው አስተዋፅኦ ለማሳድግ የገበያ ትስስር እንዲፈጠሪላቸው ጠይቀዋል:: በዞኑ ሽኮሽ ወረዳ ነዋሪ ወይዘሮ ኢፍራህ አህመድ በሰጡት አስተያየት የአከባቢው ህብረተሰብ የእጣን እና ሙጫ ምርትን ለባህላዊ ህክምናና ለሌሎች አገልግሎት እየተጠቀመ ይገኛል:: በሽኮሽ ከተማ እጣን ሙጫና ከርቤ ምርት ተረካቢ አቶ አህመድ አብዱላሂ እንዳሉት ምርቱን የሚሰባሰቡ አርብቶ አደሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ ማምጣቱን ገልፀዋል:: ከተፈጥሮ ዛፍ የሚገኘው ከርቤ፣ሙጫና እጣን ምርት ለምግብነት ለመድሃኒት ምርት ግብኣትነት እንደሚዉል የተለያዩ ጥናቶች ይጠቁማል::