Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ባህር ዳር አዲስ ከንቲባና ምክትል ከንቲባ ተሾመላት

1 969

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ባህር ዳር አዲስ ከንቲባና ምክትል ከንቲባ ተሾመላት

ባህር ዳር አዲስ ከንቲባና ምክትል ከንቲባ ተሾመላት

የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አስተዳደሩን በተሻለ መምራት የሚችሉ አዲስ ከንቲባና ምክትል ከንቲባ ሾመ።

የከተማው ምክር ቤት ለሦስት ቀናት ባካሄደው 4ኛ ዙር፣ 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤ ሹመቶችን ከመስጠት ባለፈ ዕቅዶችን ገምግሞ አጽድቋል።

በዚህም የክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር ቢሮ ኃላፊ የነበሩት አቶ አየነው በላይ ለከተማዋ በከንቲባነት ተሹመዋል።

የሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ የነበሩት አቶ ክብረት ሙሀመድ ምክትል ከንቲባ፤ ቀደም ሲል በምክትል ከንቲባነት ሲያገለግሉ የነበሩትን አቶ ምትኩ አለማየሁም ባሉበት አንዲቀጥሉ ምክር ቤቱ አጽድቋል።

የከተማዋ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብይ ኃይሉ እንደገለጹት፥ ከንቲባዎቹ የተሾሙት ያላቸውን የትምህርት ዝግጅት፣ የሥራ ልምድና ሕዝባዊ ወገንተኝነታቸውን መሰረት በማድረግ ነው።

ምክር ቤቱ ከሹመቱ በተጨማሪ የ2009 የፊዚካልና የፋይናስ እቅዶችን በጥልቀት ገምግሞ ማጽደቁን የገለጹት አቶ አብይ፥ የከተማውን ወረዳ ፍርድ ቤትና የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት እቅዶችንም በመገምገም ማጽደቁን ተናግረዋል።

ዕቅዶቹ የህዝቡን ጥያቄ መፍታት የሚያስችሉ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን ያካተቱ መሆናቸውንም አብራርተዋል።

በተለይ በጥቃቅንና አነስተኛ የሚስተዋሉ የሥራ እጥነት ችግሮችን ለመፍታት በዚህ ዓመት ከ27 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር መታቀዱን ተናግረዋል።

አቶ አብይ አያይዘው እንደገለጹት፣ ዘንድሮ ከባህር ዳር ከተማ ወደ ኤርፖርት የሚወስደውን የአስፓልት መንገድ የማስፋት ሥራ ለማከናወን ዕቅድ ተይዟል።

በከተማዋ እየተስተዋለ ያለው ሰላም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሕዝቡ ሰላሙን በማስጠበቅ የራሱን ሚና መወጣት በሚችልበት መንገድ ላይ ምክር ቤቱ መወያየቱንና አቅጣጫ ማስቀመጡንም ኃላፊው ተናግረዋል።

ከህዳር 17 እስከ 19 ቀን 2009 የተካሄደው የከተማው ምክር ቤቱ ዘጠነኛ መደበኛ ጉባኤ ዛሬ ተጠናቋል።

የባህር ዳር ከተማ የቀድሞው ከንቲባ አቶ ላቀ አያሌው ባለፈው ሳምንት በተካሄደው የአማራ ክልል ምክር ቤት ጉባኤ ለክልሉ ቴክኒክ ሙያና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው እንዲሰሩ መሾማቸው ይታወሳል።

 

 

ምንጭ፦ ኢዜአ

  1. plan cul paris says

    Ok nice girl nice tits and nice short for the company

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy