Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ብአዴን በላቀ ጉዞ የአማራ ክልልን ወደ ፊት ለማራመድ በሚያስችል ጠንካራ ቁመና ላይ ነው- አቶ ደመቀ መኮንን

0 380

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ብአዴን በላቀ ጉዞ የአማራ ክልልን ወደ ፊት ለማራመድ በሚያስችል ጠንካራ ቁመና ላይ ነው- አቶ ደመቀ መኮንን

 

ብአዴን በላቀ ጉዞ የአማራ ክልልን ወደ ፊት ለማራመድ በሚያስችል ጠንካራ ቁመና ላይ ነውአቶ ደመቀ መኮንን

የብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ብአዴን/ ዘንድሮ 36ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን የሚያከብረው የክልሉን ህዝብ ወደ ፊት ለማራመድበሚያስችለው ቁመና ላይ ሆኖ ነው አሉ የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ደመቀ መኮንን።

አቶ ደመቀ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ ላይ እንደገለፁት፥ 36ኛ ዓመት ላይ ሆኖ ድርጅቱ ብዙ ስኬቶችን ማስመዝገቡንቢመለከትም፥ በድርጅቱ ውስጥ ለላቀ እድገትና ተልእኮ በጥልቀት የመታደስ ንቅናቄው ውስጥ በመሆን ድርጃታዊ ተልእኮ የላቀ ፍሬያማ እናውጤታማ እንዲሆን ለማድረግ እየተዘጋጀ ነው።

ድርጅቱ ባለፉት 36 ዓመታት ያስመዘገባቸው ድሎች ጉዞ ሲታይ ያልተነገሩ ብዙ ታሪኮች እንዳሉም አንስተዋል።

እነዚያን ስኬቶች እና የድርጅት አቅሞችን እየተጠቀመ ድርጅቱ ለህዝብ ጥቅም እና መብት እየታገለ እዚህ ቢደርስም፥ ጉዞው አልጋ በአልጋእንዳልነበረና ከትጥቅ ትግሉ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ብዙ ፈተናዎች እንደነበሩበት ተናግረዋል።

አሁን ባለው ሁኔታ ድርጅቱ ያሉትን ችግሮች በመሰረታዊነት ፈቶ ታሪኩን የበለጠ ለመድገም እና ለቀጣዩ የእድገት እና ሽግግር የአማራን ህዝብየመምራት ብቃቱን እያጠናከረ እንዲሄድ የሚያደርግ እንደሆነም ተናግረዋል።

“የ36ኛ ዓመት በዓል በእነዚህ ማእቀፎች ውስጥ ነው የሚከበረው፤ ከታሪኩም፣ ከእለታዊ ሁኔታውም፣ ከነገ ተልእኮውም ተቃኝቶ የሚከበርይሆናል” ሲሉም አብራርተዋል።

የጥልቅ ተሃድሶ እንቅስቃሴ በኢህአዴግ ደረጃ ስምምንት በተደረሰበት አቅጣጫ መሰረት ብአዴንን በሚመለከተው ገጽታ ቀጥሎ እየተካሄደ መሆኑንሊቀመንበሩ ገልፀዋል።

በድርጅቱ ከፍተኛ አመራር ሰፊ ግምገማዎችን እና በጥልቀት ለመታደስ የሚያስችል የፖለቲካ ንቅናቄ አቀጣጥሎ በየደረጃው ተካሂዶ አሁንየመካከለኛ ደረጃ አመራር ላይ መድረሱን እና ይህም እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

ድርጅቱ በተሟላ ሁኔታ ከአመራር ጀምሮ እስከታችኛው ደረጃ ድረስ ራሱን አርሞ ለላቀ ተልዕኮ መታጠቅም የሚጠይቅ በመሆኑ ተሃድሶውተጠናክሮ ይቀጥላልም ነው ያሉት።

የአባላት የጥልቅ ተሃድሶ ንቅናቄ እንደተጠናቀቀም ወደ ህዝቡ በመሄድ የሚገኙ ግብዓቶች ተይዘው ደግሞ ድርጅቱ ለላቀ እንቅስቃሴ የሚሄድበትየቅብብሎሽ ስርዓት እንደሚዘረጋ ገልፀዋል።

“የጥልቅ ተሃድሶው እቅስቃሴው እስካሁን ድረስ በስኬት እና በታሰበው አቅጣጫ እየተካሄደ፤ የላቀ ስሜት እና ሃላፊነት እያነሳሳ መሆኑንእያረጋገጥንም ነው” ብለዋል።

የህዝብ ጥያቄዎች በፍጥነት ካልተፉ ተመልሶ ተፈጥረው ወደነበሩት ችግሮች መመለስ አይቀርም ያሉት አቶ ደመቀ፥ ድርጅቱ ራሱን አርሞ ችግሮችንበመለየት አሁን የሚፈቱትን ለመፍታት እና ቀጣይ አቅም እና ጊዜ የሚጠይቁትን ደግሞ በመለየት የመፍቻ ፍኖተ ካርታ አስቀምጦ እየሰራ መሆኑንአስታውቀዋል።

“ብዙ ሀላፊነቶችን ተሸክሞ በተግባር የተፈተነው ብአዴን የመሪነት ሚናውን በመወጣት በላቀ ጉዞ የአማራ ክልልን ወደ ፊት ለማራመድ በሚያስችልጠንካራ ቁመና ላይ ነው” ሲሉም ሊቀመንበሩ አቶ ደመቀ አረጋግጠዋል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy