አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የሃገሪቱን ሰላምና ፀጥታ ቀድሞ ወደነበረበት እየመለስ ነው:- ጠ/ሚ ኃ/ማርያም
ህዳር 8፣ 2009
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የሃገሪቱን ሰላምና ፀጥታ ቀድሞ ወደነበረበት እየመለስ መሆኑን ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ገለፁ፡፡
ጠቅላይ ሚንስትሩ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ አምባሳደሮችና ዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች ስለሃገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ገለፃ አድርገዋል፡፡
በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በሁከት ተሳትፈው ከነበሩ ግለሰቦች መካከል ከ7ዐ በመቶ በላይ የሚሆኑት ትምህርት ተሰጥቷቸው ምህረት እንደተደረገላቸው ጠቅላይ ሚንስትሩ በማብራሪያቸው ተናግረዋል፡፡
በሃገሪቱ ተፈጥሮ የነበረው አለመረጋገት የቱሪዝም ፍስቱ ላይ ተፅዕኖ ያሳደረ ቢሆንም አሁን ወደነበረበት እየተመለሰ መሆኑን ጠቅላይሚንስትሩ ገልጸዋል፡፡
በዘንድሮው በጀት ዓመት ከ12 በመቶ በላይ የኢኮኖሚ እድገት እንደሚጠበቅም ጠቅላይ ሚንስትሩ ለአምባሳደሮችና ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ተወካዮች ገልፀዋል፡፡
ሪፖርተር:- ሞገስ መኮነን