አቶ ዛዲግ አብርሃ የኢፌድሪ መንግስት ኮምንኬሽን ጉዳዮች ጽ/ ቤት ሚንስትር ዲኤታ ሆነው ተሾሙ። አቶ ዛዲግ አብርሃ ከዚህ ቀደም በታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ማስተባበርያ ፅ/ ቤት እና የፍትህና የህግ ሥርዓት ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳሬክተር ሆነው ያገለገሉ ሲሆን ወደ አዲሱ ምደባ ከመምጣታቸው በፊት በኢፌድሪ ሲቪል ሰርቪስ ሚንስቴር በአማካሪነት ሲሰሩ ቆይተዋል። አቶ ዛዲግ አብርሃ የህግ ባለሙያ ሲሆኑ በሕዝብ ዘንድ በስፋት የሚታወቁት፣ ገዢውን ፓርቲ በመወከል በተለያዩ መድረኮች በሚደረጉት ፖለቲካዊ ክርክሮች እና ከመገናኛ ብዙሃን ጋር በተያያዘ በሚሰጡ ስልጠናዎች ላይ ጥናታዊ ጽሁፎች በማቅረብ እንዲሁም ስልጠናዎች በመስጠት ነው።