Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኢህዴን/ብአዴን 36ተኛው ዓመት የምስረታ በዓል የሚታሰበው በጥልቀት የመታደስ ንቅናቄውን በማጠናከር አግባብ ነው፡፡

0 611

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የኢህዴን/ብአዴን 36ተኛው ዓመት የምስረታ በዓል የሚታሰበው በጥልቀት የመታደስ ንቅናቄውን በማጠናከር አግባብ ነው፡፡
01/03/2009

የብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤት ሃላፊና የብአዴን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ጓድ አለምነው መኮነን በዓሉን በማስመልከት ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደተናገሩት የብአዴን 36ተኛው የምስረታ በዓል የሚከበረው በስራ እና በተለያዩ የውይይት መድረኮች እንደሆነ በመግለፅ የምስረታ በዓሉ በተሃድሶ የገጠሙንን ፈተናዎች ለመፍታት በንቅናቄ ውስጥ ሁነን የምናከበረው መሆኑ ልዩ ትርጉም ይኖረዋል ብለዋል፡፡

እንደ ጓድ አለምነው ገለፃ ኢህዴን/ብአዴን የአማራ ህዝቦች የአኩሪ ታሪክና ተግባሮች ውጤት መሆኑን ገልፀው ከትጥቅ ትግሉ ማግስት ባለፉት 25 ዓመታት ዘርፈ ብዙ የገጠርና የከተማ ልማት ስራዎችን ያከናወነ መሆኑን በዚህም ቀላል ትርጉም የማይሰጣቸው ውጤቶችን ያስመዘገበ ድርጅት መሆኑን በመግለጫቸው አብራርተዋል፡፡

ድርጅቱ ባስመዘገባቸው ውጤቶች የምንኮራባቸውና ጠብቀናቸው የምንሄዳቸው መሆናቸው እንደተጠበቀ ሁኖ አሁን ወደ ተሃድሶ የገባንበት ወቅት ደግሞ ከስኬቶቻችንን ትይዩ ትልልቅ ድክሞችን ፈፅመን ህዝባችንን ቅሬታ ውስጥ ያስገባንበት ወቅት ነው ብለዋል፡፡

በዚህም በዓሉን የምናከብረው ህዝባችንን ቅሬታ ውስጥ የከተቱ ችግሮችን ለመፍታት ብሎም ከዚህ ከፍ ባለ አተያይ የክልላችንን ብሎም የሀገራችንን የሀዳሴ ጉዞ የበለጠ በሚያጠናክር አግባብ ውስጣችንን በማደስ ጥልቅ ግምገማ ንቅናቄ ውስጥ በመግባት ነው ብለዋል፡፡

ጓድ አለምነው በመግለጫቸው አክለውም ድርጅቱ ትልልቅ ድክመቶች ውስጥ የገባው በየደረጃው የሚገኘው አመራርና አባል የጠራውን መስመር በአግባቡ ካለመጨበጥና መስመሩን ከመልቀቅ ብሎም የኪራይሰብሳቢነት ጋር በተያያዘ ሰው በልፋቱና በድካሙ ተጠቃሚ እንዲሆን ከመስራት አንጻር የተፈጠረው የትግል መዳከም እንደሆነ ገልፀዋል በተሃድሶ መድረኮቹ ከተለዪት ድክመቶች መካከል ሌላኛው ዲሞክራሲያዊ ያልሆኑ ግንኙነቶች መሆናቸውን ገልፀው ህዝባችን ለጥያቄዎቹ ከድርጅቱ የሚጠብቀውን ፈጣን ምላሽ ካለማግኘቱ ጋር በተያያዘ የፈጠረውን ቅሬታና መከፋት በመጠቀም ፀረ-ሰላም ሀይሎች ባስነሱት ሁከት መተኪያ የሌለው የሰው ሂወት እና ንብረቶች ወድመዋል ብለዋል፡፡

የጥፋት ሀይሎቹ በክልላችን የፈጠሩት የጥፋት እንቅስቃሴ የአማራን ህዝቦች የሚጎዳ መሆኑን ገልፀው በዓሉን ስናከብርም ይህንን ተግባራቸውን በመታገልና በማጋለጥ ነው ብለዋል፡፡

በአንዳንድ አካባቢዎችም በከፋ የዘረኝነት ቅስቀሳ ምክንያት የዲሞክራሲያዊ ግንኙነቶችን የሚያዳክሙ ጥፋቶች መፈፀማቸውን ገልፀው የድርጅቱን የምስረታ በዓል ስናስብም አመራሩ እና አባሉ ያሉበትን መሰረታዊ ጉድለቶች በማረም እና መግባባት ለመፍጠር ከሚካሄዱ መድረኮች ጎን ለጎን የተለያዩ ሰፋፊ የውይይት መድረኮች እንዲሁም በገጠር ደግሞ ወቅቱ የሰብል ልማት የሚሰበሰብበት እንደመሆኑ መጠን በሰፊ የስራ እንቅስቃሴ ታስቦ እንደሚውል ገልፀዋል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy