Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኢትዮጵያና ቻይና በአካባቢ ሠላምና መረጋጋት በጋራ ይሰራሉ – ፕሬዚዳንት ሙላቱ

0 1,033

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኢትዮጵያና ቻይና በአካባቢ ሠላምና መረጋጋት በጋራ ይሰራሉ – ፕሬዚዳንት ሙላቱ

ኢትዮጵያና ቻይና በአካባቢ ሠላምና መረጋጋት በጋራ ይሰራሉ - ፕሬዚዳንት ሙላቱ

ኢትዮጵያና ቻይና የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር በአካባቢ ሠላምና መረጋጋት ዙሪያ በጋራ እንደሚሰሩ ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ ገለጹ።

ፕሬዝዳንቱ በቻይና ማዕከላዊ የሚሊቴሪ ኮሚሽን ምክትል ኃላፊ ጄኔራል ፋን ቻንግሎንግ የተመራውን የልዑካን ቡድን በጽህፈት ቤታቸው አነጋግረዋል።

በቆይታቸውም የሁለቱ አገራት ስትራቴጂክ ግንኙነት በሁሉም ዘርፍ በሚጠናከርበት ሁኔታ መክረዋል።

ፕሬዝዳንት ሙላቱ የሀገራቱ ግንኙነት ከመሪዎች ባለፈ በህዝብ ለህዝብ እና በቢዝነስ ለቢዝነስ የዳበረና ጠንካራ መሆኑን ለልዑካን ቡድኑ ገልጸዋል።

አገሪቷ ለያዘችው የልማት አቅጣጫም የቻይና የልማት አጋርነት የጎላ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ተናግረዋል።

ይህ መልካም ወዳጅነት ይበልጥ እንዲጠናከር በቀጣይ በአካባቢ ሠላምና መረጋጋት ዙሪያም በጋራ እንሰራለን ብለዋል።

ኢትዮጵያና ቻይና በአካባቢ ሠላም ዙሪያ በጋራ መስራታቸው ኢኮኖሚያዊ ግንኙነታቸውን ጠንካራና ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን ያስችለዋል ያሉት ደግሞ ጄኔራል ፋን ቻንግሎንግ ናቸው።

ይህን እውን ለማድረግና ግንኙነታቸው ይበልጥ እንዲጠናከር አገራቸው የበኩሏን እንደምትወጣም ነው የገለጹት።

ጀኔራሉ በቆይታቸው ከመከላከያ ሚኒስትርና ከሌሎች የስራ ኃላፊዎች ጋር እንደሚወያዩም ይጠበቃል።

 

 

ምንጭ፦ ኢዜአ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy