Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኢትዮጵያና ካናዳ ግንኙነታቸውን ይበልጥ ለማሻሻል እንደሚሰሩ ገለፁ

0 755

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

 

ኢትዮጵያና ካናዳ ግንኙነታቸውን ይበልጥ ለማሻሻል እንደሚሰሩ ገለፁ

ህዳር 2፡2009

ኢትዮጵያና ካናዳ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ይበልጥ ለማሻሻል እንደሚሰሩ ገለፁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የካናዳውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ስቴፋን ዲዮን  በጽህፈትቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያምና ሚስተር ዲዮን በሰላም ማስከበር፣ በውሃ ሃብት አጠቃቀም፣ በቢዝነስና ኢንቨስትመንት እንዲሁም በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተች መሆኗን የገለፁት ሚስተር ዲዮን የካናዳ መንግስት በሰላም ማስከበር ተልዕኮ የተሰማሩ አካላት የሥልጠና ዕድል እንዲያገኙ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በውሃ ሃብት አጠቃቀም ዙሪያም እንዲሁ ካናዳ በዘርፉ የሚሰሩ ባለሙያዎቿን በመጠቀም በኢትዮጵያ የተሻለ የውሃ አጠቃቀም እንዲኖር ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ከካናዳ ጋር በትብብር ለመሥራት ያላትን ፍላጐት ገልፀዋል፡፡

ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጭ መኖሩን ጠቅሰው የካናዳ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን ቢያፈሱ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ገልፀዋል፡፡

ከኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞ ሃገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማውጣቷን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ለዜጐች ሰብአዊ መብት አያያዝ ትልቅ ትኩረት በመስጠት የአዋጁን ተፈፃሚነት የሚከታተል መርማሪ ቡድን ተቋቁሞ እየተሰራ መሆኑን መናገራቸውን ውይይቱን የተከታተሉት የአሜሪካ ጉዳዮች  ዳይሬክተር ጄነራል አምባሣደር ተበጀ በርሄ ገልፀዋል፡፡

በተመሳሳይ ኢትዮጵያና ካናዳ በንግድ፣ በኢንቨስትመንትና በሌሎች ዘርፎች ያላቸውን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ተስማምተዋል፡፡

ሪፖርተር  :- አልጋነሽ ተካ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy