Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁ ህብረተሰቡ ያለስጋት ሠላማዊ ህይወት እንዲመራ እንዳስቻለው የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ፡፡

0 1,063

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁ ህብረተሰቡ ያለስጋት ሠላማዊ ህይወት እንዲመራ እንዳስቻለው የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ፡፡
የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዙሪያ ዛሬ በባህር ዳር ከተማ ውይይት ባካሄዱበት ወቅት በምክትል ርዕስ መስተዳደር ማዕረግ የርዕሰ መስተዳድሩ የህዝብ ግንኙት አማካሪ አቶ አለምነው መኰንን እንደገለፁት ህብረተሰቡ በተደጋጋሚ የሚያነሷቸውን ጥያቄዎች በየደረጃው ያለው አመራር ነቅሶ በማውጣት ከህዝቡ ጋር በመወያየት እንዲፈታ አቅጣጫ ተይዞ የተሰራ መሆኑን ገልፀው ህብረተሰቡ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ የተሟላ ግንዛቤ ይዞ ከሁሉም ነገር በላይ የሆነውን ሠላም እና የህግ የበላይነትን በዘላቂነት ለማረጋገጥ ከፀጥታ ሃይሉ ጋር አብሮ በመስራት ሠላምን ሊያስጠብቅ ይገባል ብለዋል፡፡
የምዕራብ ዕዝ ምክትል አዛዠ ጀኔራል መሃመድ ተሰማ በበኩላቸው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የህዝቦችን ህልውና ከጥፋት ሃይሎች የሚመክት መሆኑን ገልፀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተግባሪ አካል ህዝቡ በመሆኑ በአፈፃፀም ላይ የሚታዩ ድክመቶችን ለማስተካከል ህብረተሰቡ ከፀጥታ አካላት ጋር አብሮ በመስራት የተጀመረውን እንቅስቃሴ ማስቀጠል ይኖርበታል ብለዋል፡፡
የውይይቱ ተሳታፊ ከሆኑ የከተማው ነዋሪዎች መካከል አቶ ተስፋዬ ኩራባቸው እና አቶ ሲኖር አያሌው እንደገለፁት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መታወጁ ህብረተሰቡ በሠላም ወጥቶ በሠላም እንዲገባ እና ያለስጋት የእለት ተዕለት እንቅስቃሴውን በሠላም እንዲመራ ያስቻለ በመሆኑ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምንነት እና ተፈፃሚ በሚሆንበት ጊዜ የሚወሰዱ እርምጃዎች እና በተከለከሉ እና ባልተከለከሉ ጉዳዮች ዙሪያ የውይይት መነሻ ሃሳብ በፌደራል ፓሊስ የአማራ ክልል ኮማንድ ፖስት አባል ምክትል ኮማንደር ወንድሙ ጫማ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy