የኦትላንታው ኮንፍራስን ሰነድ አፈትልኮ ወጣ –
የአትላንታ የኦሮሞ አክቲቪስቶች ስብሰባን በተመለከተ እነ ጃዋር ስብሰባው በትልቅ ጥንቃቄና ሚስጠር ነበር የያዙት። ምንም መረጃ እንዳይወጣ። የተወሰኑ ፎቶዎች ከመልቀቅና በኦሮሞ ሜዲያ ኔቶዎርክ የተቀነጨቡ ዘገባዎችንብ ከማቅረብ ዉጭ።
ሆኖም በስብሰባው የቀረበ ሰነድ አፈትልኮ ወጥቷል። ከሰነዱ ለመረዳት እንደቻልነው፡
1) የአትላንታው ቻርተር የኢትዮጵያን አንድነት አልተቀበለም። ነጻ ኦሮሚያን ለመመስረት ወይንም በዴሞክራቲክ ኢትዮጵያ ሥር ለመሆን ፣ ወደፊት በኦሮሞ ህዝብ ዉሳኔ ነው የሚወሰነው የሚል አቋም ነው የወሰዱት። በአጭሩ አባባል የኦነግን ያረጀበትና የከሸፈበት የፖለቲክ ፕሮግራምን ነው ያጸደቁት።
2) የንቅናቄያቸው ፣ ወይም ስብስባቸው መሪ በወህኒ የሚገኘው በቀለ ገርባን አድርገዉታል። በቀለ ገርባ የመድረክ አመራር ነው። መድረክ በኢትዮጵያ አንድነት የሚያምን ስብስብ ነው። ሰዎቹ በቀለ ገርባ ይሄ አቋማቸዉን እንደማይቀበላቸው እያወቁ በስሙ መነድና በርሱ ላይ ወያኔ ያቀረበበት ክስ የበለጠ እንዲወሳሰብበት ማድረጋቸው በጣም አሳፋሪ ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ ኦፌኮ ግልጽ ምላሽ ይሰጣል ብዬ እጠብቃለሁ።
3) የሚገርመው ደግሞ የበቀለ ምክትል የሆነው ጃዋር መሐመድ ነው። በቀለ ገርባ በቀላሉ አይፈታም ከሚል ግምት ነው መሰለኝ ፣ ጃዋር በይፋ “መሪ” ሆኗል። የአትላናት ኮንፍራንስ አዘጋጅቶ፣ ሲስተማቲክ በሆነ መንገድ በይፋ የ”ኦሮሞዎች” መሪ ሆኗል።
4) እርስ በርስ የማይሰማሙ ሶስት የኦነግ አንጃዎች፣ አብረ መስራት ስለማይችሉ፣ ኦሮሚያን ለሶስት ከፍለው በዚያ የወታደራዊ እዝ እንዲያቋቁሙ ተወስኗል። የከማል ገልቹ ደርጅት በአርሲ፣ በባሌ፣ በቦረና እና በጉጂ፣ የዳዎድ ኢብሳ ቡድን በሃረረጌ፣ በወለጋ፣ በጂማ፣ በኢሊባቡር፣ የጀነራል ሃይሉ ጎንፋ ቡድን ደግሞ በሸዋ፣ ሸገርን ጨመሮ ማለት ነው።
5) ከሌሎች ኢትዮጵያዉያን ጋር አብሮ ስለመስራትና ስለመነጋገሩ ጉዳይ የተተባለ ነገር ስለመኖሩ ማወቅ አልተቻለም። ይመስለኛል በኦሮሚያ ዉስጥ የሚኖሩ ሌሎች ኢትዮጱያዉይን እንደሌሉ ነው የተቆጠረው።