ጥልቅ ተሃድሶው ጠንካራ አመራር ለመገንባት የሚያስችል መሆኑን ህወሃት ገለጸ
የተጀመረው በጥልቅ የመታደስ የትግል አቅጣጫ ህዝብን የሚያገለግልና አመኔታ ያለው ጠንካራ የፖለቲካ አመራር ለመገንባት የሚያስችል መሆኑን ሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ /ህወሃት/ አስታወቀ። የድርጅቱን ከፍተኛ አመራሮች ጥልቅ ተሃድሶ ተከትሎ በትግራይ ደቡባዊ ዞን የመካከለኛ አመራሮች ቀጣይ የተሃድሶ ግምገማ ትናንት በማይጨው ከተማ ተጀምሯል።