Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

42 ሺህ ተሳታፊዎች የተካፈሉበት 16ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በአማረ ሁኔታ ተካሄደ

0 776

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ዛሬ ህዳር 11፣2009 መነሻና መድረሻውን መስቀል አደባባይ አድርጎ የተካሄደው የዘንድሮው ታላቁ ሩጫ ውድድር በአማረ  ሁኔታ  ተጠናቋል።

በውድድሩ ሁለት አይነት የመሮጫ ማሊያ  የለበሱ 42 ሺህ የውድድሩ ተካፋዮች ተሳታፊ ሆነዋል።

ቀይ ለብሰው የሚሳተፉ ተወዳዳሪዎች ከ1 ሰአት በታች መግባት የሚችሉ ብቻ ሲሆኑ፥ አረንጓዴ የሚለብሱት ከ1 ስአት በላይ የሚገቡት ናቸው።

ቶታል ስፖንሰር ባደረገው ታላቁ ሩጫ 500 ኢትዮጵያዊያና  ሁለት የውጭ  አትሌቶች  ተሳትፈዋል።

በዚህም መሰረት የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫውን በወንዶች አትሌት አቤ ጋሻሁን ከአማራ ማረሚያ ቤት አንደኛ በመሆን የ50 ሺህብር ሽልማት አሸናፊ  ሆኗል።

ኬንያዊው አትሌት ጆሩም ሉምባሲ ሁለተኛ የወጣ ሲሆን፥ አትሌት አዱኛ ታከለ ከኦሮሚያ ፖሊስ ሶስተኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቋል።

በሴቶች በተደረገ ውድድርም አትሌት ፎቴን ተስፋዬ ከመሰቦ ስፖርት ክለብ አንደኛ በመሆን ቶታል ኢትዮጵያ  ያዘጋጀውን ሽልማት አሽንፋለች።

በዚሁ  በሴቶቹ ምድብ አትሌት ሙልዬ ደቀቦ ከኦሮሚያ ፖሊስ ሁለተኛ በመሆን ውድድሩን ያጠናቀቀች ሲሆን፥ አትሌት ታደለች በዳሶ ከኦሮሚያ ማረሚያ ቤት ሶስተኛ በመውጣት ውድድሯን ጨርሳለች ።

በውድድሩ ላይ ከአንድ እስከ ሶስት ለወጡ ለሁሉም አትሌቶች የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ከ250 በላይ የውጭ ሃገር ተሳታፊዎች ከ20 በላይ የተለያዩ ሃገራት በውድድሩ ላይ መሳተፋቸውም ተገልጿል።

የአፍሪካ ትልቁ የጎዳና ሩጫ የዘንድሮ ዋና መልዕክት “መኖር ለዚህ አበቃኝ” በሚል ከብሄራዊ የአደጋ ስጋት ቅነሳ ስራ አመራር ኮሚሽን ጋር በመተባበር ተላልፏል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy