Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በህገ ወጥ መንገድ ከሀገር ሊወጡ የነበሩ 32 ወጣቶች በመኪና አደጋ ለሞትና አካል ጉዳት ተዳረጉ

0 635

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በህገ ወጥ መንገድ ከሀገር ሊወጡ የነበሩ 32 ወጣቶች በመኪና አደጋ ለሞትና አካል ጉዳት ተዳረጉ

ታህሳስ 7፣2009

በህገ ወጥ መንገድ በሀረር በኩል ከሀገር ሊወጡ የነበሩ 32 ወጣቶች በመኪና አደጋ የሞትና አካል  ጉዳት ደረሰባቸው።

ፎቶ  – ፋይል

45 ወጣቶችን ጭኖ  በድብቅ ሲጓዝ በነበረ መኪና ላይ አደጋ ደርሶበት ነው ስድስቱ  መሞታቸውን  የሀረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ  ኮማንደር ጣሰው ቻለው የተናገሩት፤26 ደግሞ ለቀላል የአካል ጉዳት ተዳርገዋል።

ኃላፊው  እንዳሉት ወጣቶቹ  ላይ  አደጋ የደረሰው  በሌሊት ተጭነው ሲጓዙ ነው።

ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ በክልሉ 10 ሺህ ወጣቶች ከሀገር ሊወጡ ሲሉ መያዛቸውንና ወደ  መጡበት እንዲመለሱ  መደረጉንም  ኃላፊውን ጠቅሶ  የሀረሪ  ክልል ብዙሃን መገናኛ  ድርጅት ለኢቢሲ በላከው ዘገባ አመልክቷል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy