በኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ የተመራው የልዑካን ቡድን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ትናንት ሱዳን ካርቱም ገብቷል፡፡ በትናንትናው ቆይታቸው ዶ/ር ወርቅነህ በካርቱም ከሚገኙ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ሰራተኞች ጋር የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የተማከሩ ሲሆን፤ ለሱዳን ጋዜጠኞችም በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ፤ በቀጠናውና የሁለቱ ሀገራት ግንኙነትን በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በዛሬው ዕለትም በቀጠና ጉዳዮችና በሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ ከፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽርና ከሀገርቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢብራሂም ጋንዱር ጋር ይወያያሉ፡፡ በዶ/ር ወርቅነህ በተመራው የልዑካን ቡድን የጎረቤት ሀገራትና የኢጋድ እንዲሁም የፐብሊክ ዲፕሎማሲና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ጀነራሎችን ያቀፈ መሆኑ ታውቋል፡፡