Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በጥልቅ ተሃድሶው ችግሮችን ከመለየት እስከ ስልጣን ሽግሽግ ተጨባጭ ስራዎች ተሰርተዋል – ኢህአዴግ

0 491

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በጥልቅ ተሃድሶው ችግሮችን ከመለየት እስከ ስልጣን ሽግሽግ ተጨባጭ ስራዎች ተሰርተዋል – ኢህአዴግ

በጥልቅ ተሃድሶው ችግሮችን ከመለየት እስከ ስልጣን ሽግሽግ ተጨባጭ ስራዎች ተሰርተዋል - ኢህአዴግ

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) በእስካሁኑ የጥልቅ ተሃድሶ ንቅናቄ ሂደት ችግሮችን ከመለየት እስከ ስልጣን ሽግሽግ ተጨባጭ ስራዎች መስራቱን አስታወቀ።

መንግስት መስርቶ ሀገሪቱን እያስተዳደረ ያለው የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ወደ ጥልቅ ተሃድሶ ንቅናቄ ለመግባቱ የተለያዩ ምክንያቶችን ያስቀምጣል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ከጥልቅ ተሃድሶው ንቅናቄ መጀመር በፊት፥ በስልጣን ላይ ያለ አመለካከትን ለማስተካከል ራስን በጥልቀት መፈተሽ ይገባል ብለው ነበር።

በኢህአዴግ ፅህፈት ቤት የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የገጠር ዘርፍ አስተባባሪው አቶ ተፈራ ደርበው፥ የአሁኑ የመታደስ ሂደት በመጀመሪያው የመታደስ ትግበራ የታዩ ስኬቶችን መጠበቅ እና ማስፋት እንዲሁም በትግበራ ወቅት የታዩ ድክመቶችን የማረም አላማን የያዘ መሆኑን ይናገራሉ።

መነሻውን ስራ አስፈፃሚ ላይ አድርጎ ወደ ታች እየወረደ ያለው ግምገማም፥ ድርጅቱና በድርጅቱ የሚመራው መንግስት የተጋረጡበትን ችግሮች አንድ በአንድ የለየ መሆኑንም ተናግረዋል።

ችግር ተብለው ከተለዩት ጉዳዮች መካከል ስልጣንን የግል መገልገያ አድርጎ መመልከት የሚለው የችግሮቹ ሁሉ እናት መሆኑ እንደታመነበትም ያነሳሉ።

ከዚህ ባለፈ ግን የህዝብን ጥያቄ የመመለስ አቅም መዳከም፣ የኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰብ እንዲሁም የትምክህትና ጠባብነት አስተሳሰብ በአመራሩ በዋናነት የተለዩ ችግሮች መሆናቸውንም አስረድተዋል።

በግምገማው ችግሮችን ከመለየት እና ለህዝቡ በግልፅ እንዲቀርብ ከማድረግ ባለፈም፥ የተለዩ ችግሮችን አመራሩ በባለቤትነት እንዲወስዳቸው ግለ ሂስ መደረጉንም ነው ያነሱት።

በፌደራል መንግስት የተደረገው የካቢኔ አባላት ሹም ሽርም የፖለቲካ ግምገማው ውጤት እና እርምጃ እንደሆነም ገልጸዋል።

ጥልቅ ተሃድሶው በፓርቲ ውስጥ ያለ ሃላፊነት ለመንግስት ሹመት እንዳማያበቃ በተግባር ያረጋገጠ ነውም ብለዋል።

ጥልቅ ተሃድሶው በቀጣይ ወደ ታችኛው መዋቅር ይወርዳል ያሉት አቶ ተፈራ፥ በመላ ሀገሪቱ ህዝቡ በቀጥታ የሚሳተፍበት የውይይት መድረክ ለመፍጠር ዝግጅት መጠናቀቁንም ነው የተናገሩት።

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy