Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

አዲሱ የኤች አይ ቪ ክትባት ሙከራ በደቡብ አፍሪካ ተጀመረ

0 2,661

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

አዲሱ የኤች አይ ቪ ክትባት ሙከራ በደቡብ አፍሪካ ተጀመረ

አዲሱ የኤች አይ ቪ ክትባት ሙከራ በደቡብ አፍሪካ ተጀመረ

በአለማችን የኤች አይ ቪ ስርጭትን በተመለከተ ግብዛቤ ለመፍጠር የፈረንጆቹ ታህሳስ 1 ቀን የአለም ኤድስ ቀን ተብሎ ታስቦ ይውላል።

በዚሁ እለት የኤች አይ ቪ ምርመራን የሚያበረታቱ እና ስለ በሽታው መንስኤ እና መተላለፊያ መንገዶች የሚያስረዱ ፅሁፎች ይበተናሉ፤ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራሞችም ይከናወናሉ።

ኤድስ እስካሁን 35 ሚሊየን የአለማችን ህዝብ ለህልፈት ዳርጓል። በየአመቱም 2 ሚሊየን ሰዎች በቫይረሱ ይያዛሉ።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መረጃ እንደሚያሳየው በየአመቱ ከ1 ሚሊየን በላይ ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያልፋል።

የአለም ኤድስ ቀን መከበር ከጀመረበት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ1988 ጀምሮ የተለያዩ ተግባራት ተከናውነዋል።

በቫይረሱ መያዝ እንደ ርግማን ከሚቆጠርባቸው ሀገራት ጀምሮ የሰለጠኑት ሀገራት የቫይረሱን ስርጭት ለመቀነስ ከፍተኛ ስራ ሰርተዋል።

የኤች አይ ቪ ቫይረስ በደማቸው ውስጥ የሚገኝባቸው እናቶች ጤናማ ልጅ መውለድ እንዲችሉ መደረጉ ለዚህ አንዱ ማሳያ ነው።

የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የሚያስችሉ መድሃኒቶች ጥቅም ላይ መዋልም የበርካቶችን ህይወት ታድጓል።

በአለማችን እስካሁን ከ18 ሚሊየን በላይ ሰዎች የፀረ ኤች አይ ቪ መድሃኒቶችን በመውሰድ ላይ መሆናቸውን ነው መረጃዎች የሚያሳዩት።

በአሁኑ ወቅትም ተመራማሪዎች ለበሽታው አዲስ ክትባት እየሰሩ መሆኑ ተነግሯል።

አዲሱ የኤች አይ ቪ ክትባትም በደቡብ አፍሪካ ከትናንት ጀምሮ ሙከራ እየተደረገበት ነው።

ከ2009 ወዲህ ሰፊ ጥናት የተደረገበት አዲሱ የኤች አይ ቪ ክትባት በ5 ሺህ 400 ለወሲብ ቅርብ የሆኑ ወጣቶች ላይ ይሞከራል ተብሏል።

የክትባቱ ውጤታማነት ጥናት የሚደረግባት ደቡብ አፍሪካ ከ7 ሚሊየን በላይ ዜጎቿ የኤች አይ ቪ/ኤድስ ተጠቂ ናቸው።

የኤች አይ ቪ ቫይረስ በፈረንጆቹ 1983 መታየት ከጀመረ ወዲህ እስካሁን ውጤታማ ክትባት ለማግኘት የተደረገው ጥረት አልተሳካም።

እንደ አውሮፓውያኑ በ2009 በታይላንድ የተሞከረው አዲሱ የኤች አይ ቪ ክትባት በደቡብ አፍሪካም የሚኖረው ውጤት ከአራት አመት በኋላ ይታወቃል ተብሏል።

 

ምንጭ፦ http://cctv-africa.com/

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy