የደቡብ ክልል ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን አፀደቀ
ምክር ቤቱ አስቸኳይ ስብሰባውን ሲያካሂድ ከዚህ ቀደም በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማእረግ የክላስተር የነበሩ ሹመቶች እንዲቀሩ ወስኗል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደሴ ዳልኬ ለምክር ቤቱ ጉባኤ በማቅረብ ከተሾሙት መካከል ዘጠኙ አዲስ ተሿሚዎች ሲሆኑ፥ ከእነዚህም ሰባቱ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚያስተምሩና በምርምር ማዕከላት በተመራማሪነት የሰሩ ናቸው።
ርዕሰ መስተዳደሩ በተዋቀረው አዲስ ካቢኔ ውስጥ የተመደቡበት አመራሮች የስራ ውጤታማነታቸው፣ ታማኝነታቸውና ያላቸው ታታሪነት መታየቱንና ስድስቱ ባሉበት እንዲቀጥሉ፤ አምስቱ ወደሌላ ሴክተር እንዲሸጋሸጉና ዘጠኙ አዲስ ተሿሚዎች መሆናቸውን ገልጸዋል።
አዳዲስ የተሾሙ አመራሮች
1. ዶ/ር አብረሀም ሀላላ – የጤና ቢሮ ኃላፊ
2. ዶ/ር እሼቱ ከበደ – የትምህርት ቢሮ ኃላፊ
3. ዶ/ር ኢንጅነር ነጋሾ ዋጌሾ – የውሀ፣ መስኖ ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ
4. ዶ/ር አክመል መሀመድ – የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ
5. ዶ/ር ሀቢብ ጀማል – የእንሰሳትና አሳ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ
6. ዶ/ር ጌትነት በጋሻው – የንግድና ኢንደስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ
7. ወ/ሪት ትዝታ ፍቃዱ – የፍትህ ቢሮ ኃላፊ
8. አቶ ሰለሞን ኃይሉ – የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ
9. አቶ ንጉሴ አስረስ – የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ
አዲስ ቢሮ የቀየሩ አመራሮች
1. አቶ መለሰ አለሙ – ምክትል ርዕሰ መስተዳደርና የፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ
2. አቶ ክፍሌ ገ/ማርያም – የከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ ኃላፊ
3. አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ – የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ
4. ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን – የሴቶችና ህጻናት ቢሮ ኃላፊ
5. አቶ አድማሱ አንጎ – የፀጥታና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ
6. አቶ ታምራት ዲላ – የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ
በነበሩበት የቀጠሉ
1. አቶ ጥላሁን ከበደ – የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ
2. አቶ ፍቃደ ስላሴ ቤዛ – የቴክኒክና ሞያ ቢሮ ኃላፊ
3. አቶ ንጋቱ ዳንሳ – የአርብቶ አደር ቢሮ ኃላፊ
4. ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ – የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ
5. አቶ መሳፍንት አለማየው – የኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ
ተሿሚዎቹ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ሙሉጌታ አጎ አማካኝነት ቃለ መሃላ ፈፅመው ምክር ቤቱ ያካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ተጠናቋል።