Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ዶ/ ር መረራ ጉዲና በኢትዮጵያ የታወጀውን የአስቸኳይ የጊዜ አዋጅ መመርያ አንቀፅ 2ቁጥር 1 በመተላለፋቸው በቁጥጥር ስር ዋሉ።

1 629

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ዶ/ ር መረራ ጉዲና በኢትዮጵያ የታወጀውን የአስቸኳይ የጊዜ አዋጅ መመርያ አንቀፅ 2ቁጥር 1 በመተላለፋቸው በቁጥጥር ስር ዋሉ። ዶ/ ር መረራ ጉዲና የአስቸኳይ የጊዜ አዋጁን መመርያ አንቀፅ 2 ንኡስ ቁጥር 1 የሚደነግገውን በመጣሳቸው ምክንያት ትናንት ማምሻውን ከውጭ ሀገር ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ በቦሌ የአውሮፕላን ማረፍያ በኮማንድ ፖስቱ በቁጥጥር ስር ውለዋል። የቀድሞ የኦብኮ እና የአሁኑ ኦፌኮ ሊቀመንበር እና የተቃዋሚ ፓርቲን በመውከል የፓርላማ አባል የነበሩ ሲሆኑ በምርጫ 2002 እና 2007 በተደረገው ሀገር አቀፍምርጫ የተቃዋሚ ፓርቲን በመወከል ተወዳድረው ራሳቸውን ሳይመረጡ ቀርተዋል። ዶ/ር መረራ ጉዲና በደርግ ስርአት የመኢሶን አባል የነበሩ እና በስርአቱ ለ8 አመታት ታስረው ተፈተዋል። ከደርግ ውድቀት ቡሀላ ኢህአዴግ ሀገሪቱን መምራት ከጀመረ ቡሀላም የተቃዋሚ ፓርቲ አባል እና አመራር በመሆን ተንቀሳቅሰዋል። ዶ/ር መረራ ጉዲና በአዲስ አበባ ዪኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር የነበሩ እና ባለመስማማት ከስራ የተሰናበቱ ናቸው። ዶክተር መረራ በቅርቡ በኢትዮጵያ የታወጀውን የአስቸኳይ የጊዜ አዋጅ መመርያ አንቀፅ 2ቁጥር 1 ላይ የተደነገገው እና በሽብር ከተሰየሙ ድርጅቶች እና ፀረ ሰላም ቡድኖች ጋር ማናቸውንም ግኑኝነት ማድረግ የሚለውን በመጣስ በቤልጅየም ብራሰልስ የአውሮፓ ህብረት ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ተሳትፈው በመንግስት አሸባሪ ብሎ ከፈረጀው የግንቦት 7 አመራርና አባላት ጋር የነበራቸው ግንኙነት መሰረት ትናንት ማምሻውን ወደ አዲስ አበባ ሲገቡ በቦሌ አውሮፕላን ማረፍያ በኮማንድ ፖስቱ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

  1. yaynshet Gebremedhn says

    ዶክትሬት ልማር ዕቅድ ነበረኝ ፡ ነገር ግን እንደ ዶ/ መራራ “ዶክቶርነቴ የሚመጣኝ ችግር የማትነትንልኝ ኮሆነች የትምህርት ዕቅዴ ትቼ ወደ ኣርብቶአደረነቴ ልዋፈር ወሲኜ አለሁ !!”

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy