Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ም/ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ግንባታቸው የተጠናቀቁ ተቋማትን ጎበኙ

0 1,128

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ም/ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ግንባታቸው የተጠናቀቁ ተቋማትን ጎበኙ

ህዳር 26፡2009

ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ግንባታቸው የተጠናቀቁ ተቋማትን ጎበኙ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ደመቀ መኮንንና የፌደራል አርብቶ አደር ልማት ጉዳዮች ሚንስትር አቶ ካሣ ተክለብርሀን ከኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዲ መሀመድ ኡመር እንዲሁም ልዩ ድጋፍ የሚሹ ክልሎች የቦርድ አባላት ጋር የቀብሪደሀር ሆስፒታል፣ አየር ማረፊያ የመስኖ፣ ግድበና ሌሎች የትምህርት ተቋማትን ጎብኝተዋል፡፡

በክልሉ ውሀን ማዕከል አድርጎ የተገነባው የመስኖ ግድብ ግንባታ ዘጠኝ ሺህ ሄክታር መሬት የማልማት አቅም ያለው ሲሆን የክልሉ አርብቶ አደሮች በሰፊ የእርሻ ሥራ ላይ እንዲሰማሩ ሚናው የጎላ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ ተናግረዋል፡፡

አቶ ደመቀ መኮንን በጉብኝቱ ወቅት እንዳሉት እንደነዚህ አይነት የመሠረተ ልማት ግንባታዎች በክልሉ አቅም መገንባታቸው ክልሉ ለልማትና ለዕድገት ያለውን ቁርጠኝነት አመላካች ነው፡፡

መረጃው ያደረሰን  የክልሉ መገናኛ ብዙኃን ነው፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy