በህገ ወጥ መንገድ ከሀገር ሊወጡ የነበሩ 32 ወጣቶች በመኪና አደጋ ለሞትና አካል ጉዳት ተዳረጉ
ታህሳስ 7፣2009
በህገ ወጥ መንገድ በሀረር በኩል ከሀገር ሊወጡ የነበሩ 32 ወጣቶች በመኪና አደጋ የሞትና አካል ጉዳት ደረሰባቸው።
ፎቶ – ፋይል
45 ወጣቶችን ጭኖ በድብቅ ሲጓዝ በነበረ መኪና ላይ አደጋ ደርሶበት ነው ስድስቱ መሞታቸውን የሀረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ጣሰው ቻለው የተናገሩት፤26 ደግሞ ለቀላል የአካል ጉዳት ተዳርገዋል።
ኃላፊው እንዳሉት ወጣቶቹ ላይ አደጋ የደረሰው በሌሊት ተጭነው ሲጓዙ ነው።
ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ በክልሉ 10 ሺህ ወጣቶች ከሀገር ሊወጡ ሲሉ መያዛቸውንና ወደ መጡበት እንዲመለሱ መደረጉንም ኃላፊውን ጠቅሶ የሀረሪ ክልል ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ለኢቢሲ በላከው ዘገባ አመልክቷል።