Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በአርብቶ አደር አካባቢዎች የድርቅ ስጋትን ለመቀነስ ለመስኖ ልማት ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል፡- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ

0 792

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በአርብቶ አደር አካባቢዎች የድርቅ ስጋትን ለመቀነስ ለመስኖ ልማት ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል፡- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ

ህዳር 25፣ 2009

በአርብቶ አደር አካባቢዎች የድርቅ ስጋትን ለመቀነስ፤ ለመስኖ ልማት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተናገሩ።

የፌዴራል ልዩ ድጋፍ ቦርድ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የተለያዩ የልማት ስራዎችንና የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎችን በመጎብኘት ላይ ይገኛል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉብኝቱ ወቅት እንደገለጹት በአርብቶ አደር አካባቢዎች የሚስተዋለውን የድርቅ ስጋት ለመቀነስ ለመስኖ ልማት ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል።

በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል እየተከናወኑ ያሉ የመስኖ ልማት ስራዎች ለዚህ ማሳያ መሆናቸውንም ገልጸዋል።

ባለፉት ሁለት ዓመታት በመስኖ የበቆሎና የሰሊጥ ምርትን ጨምሮ የተለያዩ ተስፋ ሰጪ የልማት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

በቦረና፣ ጉጂና ሌሎች አካባቢዎች የሚስተዋለውን የድርቅ ስጋት ለማስወገድ ተመሳሳይ ስራ ይከናወናል ብለዋል።

ለእንስሳት በቂ መኖ ማቅረብ እንዲቻል በቂ መኖ ከማይገኝባቸው አካባቢዎች መኖ ወዳለው ቦታ እንዲንቀሳቀሱም ይደረጋል ነው ያሉት።

“በዚህም መሰረት አሁን እየተስተዋለ ያለው ድርቅ ከእጃችን ሳይወጣ ያለንን ልምድ ተጠቅመን በቁጥጥር ስር እናውለዋለን” ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

የፌደራልና አርብቶ አደር ልማት ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ካሳ ተክለብርሃን በበኩላቸው በክልሉ ተስፋ ሰጪ የልማት ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ታዳጊ ክልሎች በልዩ ድጋፍ አማካኝነት ልማታቸውን የማመጣጠን ስራ ውጤት እያሳየ መሆኑንም ገልጸዋል።

በክልሉ በራስ አቅም እየተከናወኑ ባሉ የልማት ስራዎች ዜጎች ተጠቃሚ በመሆናቸው የህብረተሰቡ ለልማት የመነሳሳት መንፈስ በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯልም ነው ያሉት።

የመስኖ ልማት ከተጎበኘላቸው ከፊል አርሶ አደሮች መካከል የጎዴ ወረዳ ነዋሪ ወይዘሮ ሀሊማ መሃመድ የስድስት ልጆች እናት ሲሆኑ ላለፉት ስድስት ዓመታት ህይወታቸውን በከፊል አርብቶ አደርነት ሲመሩ መቆየታቸውን ተናግረዋል።

መንግስት ባመቻቸው የመንደር ማሰባሰብ መርሃ ግብር ባሉበት አካባቢ የመስኖ ልማት በማከናወን ላይ ይገኛሉ።

በመስኖ ልማት ስራው ቦቆሎ፣ ሰሊጥ፣ አትክልትና ፍራፍሬ እያመረቱ ሲሆን በአኗኗራቸው ላይም ትልቅ ለውጥ እያመጡ መሆኑን ተናግረዋል።

በኑሮ ሂደት የቁጠባ ባህላቸውን እያዳበሩ ሲሆን የጤና ተቋማትን ጨምሮ ሌሎች መሰረተ ልማቶች ተሟልተውላቸው ተጠቃሚ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

የፌዴራል ልዩ ድጋፍ ቦርድ አባላት በእስካሁኑ ጉብኝታቸው የቀብሪ ደሃር መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጅ፣ የቀብሪ ደሃር ጠቅላላ ሆስፒታል፣ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋም እንዲሁም የመስኖ ልማት ግድቦችን ጎብኝተዋል።

ጉብኝቱ በነገው እለትም እንደሚቀጥል ይጠበቃል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy