Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኢትዮጵያና አሜሪካ በዲሞክራሲ፣ በመልካም አስተዳደር እና በሰብአዊ መብት ጉዳዮች ላይ መከሩ

0 617

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኢትዮጵያና አሜሪካ በዲሞክራሲ፣ በመልካም አስተዳደር እና በሰብአዊ መብት ጉዳዮች ላይ መከሩ

ኢትዮጵያና አሜሪካ በዲሞክራሲ፣ በመልካም አስተዳደር እና በሰብአዊ መብት ጉዳዮች ላይ መከሩ

ኢትዮጵያና አሜሪካ በዲሞክራሲ፣ በመልካም አስተዳደር እና በሰብአዊ መብት ጉዳዮች ላይ የሁለትዮሽ ምክክር አካሄዱ።

7ኛው የዲሞክራሲ፣ የመልካም አስተዳደርና የሰብአዊ መብት ጉዳዮች የስራ ቡድን ስብሰባ በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

በውይይቱ የኢፌዲሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ እና በአሜሪካ የዲሞክራሲ፣ የሰብአዊ መብት እና ስራ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ቶም ማሊኖውስኪ ተገኝተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሂሩት ዘመነና በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ጉዳይ ፈጻሚ ፒተር ቭሮማን በጋራ በሊቀመንበርነት የመሩት ስብሰባ በውጤታማነት እንደነበርም ነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያስታወቀው።

የሁለቱ ሀገራት ተወካዮች የመልካም አስተዳደርና የሰብአዊ መብት ጉዳዮችን በሚመለከት በግልጽነትና በስፋት የሚወያዩበትን መልካም አጋጣሚ የፈጠረ መሆኑንም ጠቁሟል።

የሁለቱ ወገኖች ምክክር ሰፋ ያሉ ጉዳዮችን የዳሰሰ ሲሆን ከእነዚህ መካከል ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ ለሁለቱ ምክር ቤቶች ባሰሙት ንግግር እንደጠቀሱት የኢትዮጵያ መንግስት የምርጫ ስርዓቱን ለማሻሻል ያለው ዝግጁነት፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈጻጸም ለህገ መንግስታዊ መብቶችና ግዴታዎች መከበርና ለውይይት የሚሰጠው ትኩረት፣ የመገናኛ ብዙሃን  እንዲያድጉና እንዲጠናከሩ የሚያስፈልገው ድጋፍ፣ መሰረታዊ ነጻነቶች በተጠበቁበት ሁኔታ የጥላቻ ንግግሮችን መዋጋት የሚቻልባቸው ስልቶች፣ መልካም አስተዳደርን ለማጠናከር የሲቪክ ማህበረሰቡ ሚናና አስፈላጊነት እንዲሁም በአሜሪካ የሰብአዊ መብት ሪፖርት ዙሪያ የተደረጉ ውይይቶች ተጠቃሾች ናቸው።

ሁለቱም ወገኖች ባወጡት መግለጫ የስራ ቡድኑ ስብሰባ ያለማቋረጥ እንዲቀጥል መግባባት ላይ መድረሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያደረሰን መረጃ ያመለክታል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy