ኢትዮጵያ ከሌሎች ሀገራት ጋር ያላትን የንግድ እና የኢንቨስትመንት ግንኙነት አጠናክራ ትቀጥላለች- ዶ/ር ወርቅነህ
ዶክተር ወርቅነህ ትናንት ምሽት መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ካደረጉ የውጭ ሀገራት አምባሳደሮች፣ አለም አቀፍ ደርጅቶች እና ተቋማት ሃላፊዎች ጋር የትውውቅ ፕሮግራም አካሂደዋል።
ሚንስትሩ በዚሁ ጊዜም፥ በአሁኑ ወቅት መንግስት የንግድ እና ኢንቨስትመንት ዘርፉን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ሲሉም ተናግረዋል።
ሀገሪቱ የምታካሄደዉ የኢንደስትሪ ልማት ግንባታም ለዚህ ዘርፍ እደገት የራሱን አስተዋፅኦ እያበረከተ መሆኑንም ሚኒስትሩ ገልፀዋል።
የኢንደስትሪ ፓርኮች የውጭ ቀጥታ ኢንቭስተመንትን እየሳቡ እና ለበርካታ ወጣቶች የስራ እድል እየፈጠሩ መሆኑንም ዶክተር ወርቅነህ ተናግረዋል።
ዶከተር ወርቅነህ አምባሳደሮቹን እና የአለም አቀፍ ተቋሟት ሃላፊዎቹን ኢትዮጵያ የምታካሂደውን ሁሉን አቀፍ የልማት እንቅስቃሴ ለመደገፍ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረዉ አንዲቀጥሉ ጠየቀዋል።
ሚንስትሩ አያይዘውም፥ ኢትዮጵያ በአህጉራዊ እና በአለም አቀፍ ደረጃ ሰላም እና መረጋጋት እንዲፈጠር የምታደርገዉን አስተዋፅኦም አጠናክራ ትቀጥላልች ብለዋል።
በስላባት ማናየ