Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኤች.አይ.ቪን በ86 በመቶ ይከላከላል የተባለው መድሃኒት ሙከራ ሊደረግበት ነው

0 799

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኤች.አይ.ቪን በ86 በመቶ ይከላከላል የተባለው መድሃኒት ሙከራ ሊደረግበት ነው

ኤች.አይ.ቪን በ86 በመቶ ይከላከላል የተባለው መድሃኒት ሙከራ ሊደረግበት ነው

በኤች አይ ቪ የመጠቃት እድልን በ86 በመቶ ይቀንሳል የተባለው መድሃኒት በእንግሊዝ ሀገር በሙከራ ደረጃ ሊሰጥ መሆኑ ተነግሯል።

የእንግሊዝ ብሄራዊ የጤና አገልግሎት ተቋም እንዳስታወቀው፥ “ፕሪፕ” የሚል መጠሪያ ያለው ይህ መድሃኒት በአጭር ጊዜ ለታማሚዎች መሰጠት ይጀመራል።

ለሶስት ዓመታት በሚቆየት የኪሊካል ሙከራ ጊዜም መድሃኒቱን ለ10 ሺህ ሰዎች በመስጠት ሙከራ እንደሚያደርግምበትም ተቋሙ አስታውቋል።

“Pre-exposure prophylaxis ወይም Prep” በየእለቱ የሚዋጥ መድሃኒት ሲሆን፥ ኤች.አይ.ቪ ቫይረስ በሰውነት ውስጥ ተስፋፍቶ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ መከላከል የሚችል ነው ተብሏል።

መድሃኒሩን የሚወስድ ሰው በወር 400 ዩሮ እንደሚከፍልም ነው የእንግሊዝ ብሄራዊ የጤና አገልግሎት ተቋም ያስታወቀው።

መድሃኒቱ በኤች.አይ.ቪ ቫይረስ የመጠቃት እድልን በ86 በመቶ እንደሚቀንስም ነው ተቋሙ የገለፀው።

መድሃኒቱ በሙከራ ደረጃም ቢሆን ስራ ላይ እንዳያውል የተለያዩ ክልከላዎች ሲጣሉበት የነበረው የእንግሊዝ ብሄራዊ የጤና አገልግሎት ተቋም ባወጣው መግለጫ፥ መድሃኒቱ ፍቱን ስለመሆኑ ማረጋገጫ አለኝ ብለዋል።

ሆኖም ግን አሁንም ያልተመለሱ ጥያቄዎች አሉ የተባለ ሲሆን፥ በተለይም መድሃኒቱን በስፋት እንዴት ጥቅም ላይ ማዋል ይቻላል የሚለው ሌላ ተጨማሪ ስራ የሚያስፈልገው መሆኑም አስታውቋል።

በቅርቡ ሙከራ ይደረግባቸዋል የተባሉ 10 ሺህ ሰዎችም መድሃኒቱን እንዴት መውሰድ አለበት እና ለምን ያክል ጊዜ መወሰድ አለበት የሚለውን ለመለየት እንደሚረዳም ተገልጿል።

በእንግሊዝ ብሄራዊ የጤና አገልግሎት ተቋም የኤች.አይ.ቪ ጉዳዮች ዳይሬክተር ዶክተር ላን ዊሊያምስ፥ ለአሁን ሙከራው የሚደረግባቸው ሰዎች የበለጠ ለኤች.አይ.ቪ ተጋልጠዋል የተባሉ ሰዎች ላይ ነው ብለዋል።

በትሬንስ ሀይጅን ትረስት ሜዲካል ዳይሬክረት የሀኑት ዶክተር ሚሼል ብራድሌይ በበኩላቸው፥ “ፕሪፕ” መድሃኒት ፍቱን ስለመሆኑ በርካታ ማረጋገጫዎች አሉ፤ ሆኖም ግን አሁን የሚደረገው ሙከራ መድሃኒቱ በሰዎች የእለት ተእለት ኑሮ ውስጥ እንዴት ተግባራዊ መደረግ አለበት የሚለውን ለመለየት ነው ብለዋል።
አሁንም ግን ከሙከራው ጋር በተያያዘ የተግባር ሙከራው ውጤት ምን ሊሆን ይችላል፣ ለኤች.አይ.ቪ የተጋለጡ ሰዎች በምን መልኩ መድሃኒቱን ማግኘት ይችላሉ፣

ከሙከራው በኋላ ምን ሊፈጠር ይችላል የሚሉት አሁንም መልስ የሚሹ ነገሮች ናቸው ሲሉም ዶክተር ሚሼል ተናግረዋል።

በእንግሊዝ ናሽናል ኤድስ ትረስት ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ዲቦራህ ጎልድ፥ መድሃኒቱ በሙከራ ደረጃ እንዲሰጥ ፍርድ ቤት ቀርበን ተከራክረን በማሸነፋችን በጣም ደስ ብሎኛል፤ አሁን ቀጣዩ ስራችን ፕሪፕ መድሃኒትን ለሚለፈልጉ በስፋት ማቅረብ ላይ ነው ብለዋል።

በተባበሩት መንግስት ኤች አይቪ ኤድስ ማስበታበሪያ ድርጅት (UNAIDS) ያወጣው ሪፖርት እንደሚያመለክተው እስካሁን በዓለም ዙሪያ 78 ሚሊየን ሰዎች ኤች.አይ.ቪ ቫይረስ ተጠቅተዋል።

በዓለም ዙሪያ እስከአሁን 35 ሚሊየን ሰዎች ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ሳቢያ ህይወታቸውን ማጣታቸውንም ሪፖርቱ ያመለክታል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy