Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የመንግስት አመራሮችን ጨምሮ በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ 130 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

0 566

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የመንግስት አመራሮችን ጨምሮ በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ 130 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የመንግስት አመራሮችን ጨምሮ በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ 130 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ 130 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

መንግስት የህዝቡን ጥያቄ ለመመለስ እና ለመልካም አስተዳደር እጦት ምክንያት የሆኑ አመራር እና ፈጻሚ አካላትን ለማረም የጥልቅ ተሃድሶ ግምገማ እያደረገ ይገኛል።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንም የመንግስት ጥልቅ ተሃድሶን ተንተርሶ ባለፉት ጥቂት ወራት ከህዝብ፣ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጥቆማዎች ደርሰውታል።

በዚህም ፖሊስ ከህብረተሰቡ የደረሱትን 260 ጥቆማዎች ተቀብሎ እንዲጣሩ ማድረጉን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀኔራል ልዩ አማካሪ ኮማንደር ደስታ አስመላሽ ተናግረዋል።

በእንዲሀ መልኩ የህብረተሰቡን ጥቆማዎች ተቀብሎ ማጣራት የጀመረው ኮሚሽኑ፥ አሁን ላይ ከ130 በላይ ተጠርጣሪዎችን በከባድ የሙስና ወንጀል ተገቢው ማስረጃ ቀርቦ እንዲጣራ ተደርጓል ብለዋል።

ተጠርጣሪዎቹ የመንግስት አመራሮች፣ ባለሙያዎች እና የተለያዩ ግለሰቦች መሆናቸውንም ነው ኮማንደር ደስታ የተናገሩት።

ተጠርጣሪዎቹ ከመንግስት እቃ ግዥ፣ የቤቶች ልማት፣ መሬት ልማት፣ ባንክ ስራዎች እና ከሸር ኩባንያዎች፥ የታክስ ማጭበርበር እና የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል በሚል በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ገልጸዋል።

ይህን ተከትሎ ፖሊስ በወሰደው እርምጃ 13 የሃብት እና ንብረት እገዳ ማድረጉን ይገልጻሉ።

8 ትላልቅ ሸር ኩባንያዎች፣ 2 ፋብሪካዎች፣ 4 ህንፃዎች፣ 22 መኖሪያ ቤቶች እና 49 ተሽከርካሪዎች ላይ በተጨማሪነት እገዳ ተጥሏልም ነው ያሉት።

ኮሚሽኑ ከህብረተሰቡ ከደረሱት ጥቆማዎች ባሻገር በፌደራል ስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በኩል ተይዘው የነበሩ ከ102 በላይ መዝገቦች ምርመራ ተካሂዶባቸው ለፍርድ ቤት መለላካቸውንም አስረድተዋል።

ከባድ የሙስና ወንጀሎች በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ቀለል ያሉት ደግሞ የአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር ፖሊስ ኮሚሸን፥ በውክልና ጥቆማዎችን ተከትለው መረጃዎችን የማጣራት እና የመመርመር ስራዎችን እየሰሩ ነው።

በቅርቡም የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከህብረተሰቡ የደረሰውን ጥቆማ ተከትሎ በወሰደው ዘመቻ 125 በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦችን፥ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ በማካሄድ ክስ እንዲመሰረትባቸው መደረጉን ልዩ አማካሪው አስታውሰዋል።

ኮሚሽኑ ሙስናን በተመለከተ ለሚደርሰው ጥቆማ ተገቢውን ምላሸ ለመስጠት፥ የአደረጃጀት እና የሰው ሃይል ምደባውን በተገቢው መንገድ እንዳጠናቀቀም ገልጿል።

በቀጣይም ህብረተሰቡ የሙስና ወንጀሎችን ለማጋለጥ በአካል በመቅረብ ወይም በኮሚሸኑ ስልክ ቁጥሮች ደውሎ በመጠቆም አጋርነቱን እንዲሳይም ጠይቋል።

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy