Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በደንብና አዋጅ ረቂቆች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

0 439

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በደንብና አዋጅ ረቂቆች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

ታህሳስ 7፣ 2009

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በመንገድ ትራስፖርት ትራፊክ መቆጣጠሪያ ረቂቅ ደንብና በፓሪስ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት ማጽደቂያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ።

ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 18ኛ መደበኛ ስብሰባ በረቂቅ ደንቡ ላይ ከተወያየ በኋላ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ እንዲወጣና በስራ ላይ እንዲውል ሲወስን፤ ረቂቅ አዋጁን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መርቷል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ የመንገድ ትራንስፖርት ለአንድ አገር ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ዕድገት ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።

የትራንስፖርት ንዑስ ዘርፋን የተሳለጠ ማድረግ ካልተቻለ በዜጎች ህይወትና በአገር ሃብት ላይ የጎንዮሽ ጉዳት የሚያስከትል መሆኑን ጠቁሞ፤ አሁን ካለው የትራፊክ መጨናነቅ አኳያ የመንገድ ትራፊክ መቆጣጠሪያ ደንብን ማሻሻል አስፈላጊ መሆኑ በመግለጫው ተመልክቷል።

በመሆኑም ምክር ቤቱ በትራንስፖርት ሚኒስቴር ተዘጋጅቶ በቀረበው ረቂቅ ደንብ ላይ ከተወያየ በኋላ በስራ ላይ እንዲውል ወስኗል ብሏል ኢዜአ በዘገባው።

ምክር ቤቱ የፓሪሱን የአየር ንብረት ስምምነት ለማጽደቅ በተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ ውሳኔ አሳልፏል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy