Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የቻይናው ፖሊ ግሩፕ ኮርፖሬሽን በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ኦጋዴን አካባቢ የሚያከናውነው የጋዝና የቤንዚን ፍለጋ ሥራ ውጤት እያስገኘ መሆኑን ገለጸ።

0 1,112

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የኦጋዴን ጋዝና ቤንዚን ፍለጋ ውጤት እያስገኘ ነው —ፖሊ ግሩፕ ኮርፖሬሽን

አዲስ አበባ ታህሳስ 6/2009 የቻይናው ፖሊ ግሩፕ ኮርፖሬሽን በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ኦጋዴን አካባቢ የሚያከናውነው የጋዝና የቤንዚን ፍለጋ ሥራ ውጤት እያስገኘ መሆኑን ገለጸ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የፖሊ ግሩፕ ኮርፖሬሽን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

የኮርፖሬሽኑ ምክትል ሊቀመንበር ቡ ዩሎንግ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት በኦጋዴን አካባቢ የጋዝና የቤንዚን ፍለጋ ሥራው ውጤት እያስገኘ ነው።

በ 3 ነጥብ 7 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወጪ እየተከናወነ ያለው የፍለጋ ፕሮጀክት በእስካሁኑ ቁፋሮ ተስፋ ሰጪ እንደሆነም ተናግረዋል።

በቀጣይም የፍለጋ ሥራው ይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው ምክትል ሊቀመንበሩ የገለጹት።

ኮርፖሬሽኑ ከጋዝና ቤንዚን ፍለጋ ሥራ ባለፈ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ለኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ሽግግር እያስገኘ እንደሆነም ጠቅሰዋል።

ከኢትዮጵያ መንግሥት ለኮርፖሬሽኑ አስፈላጊ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ተናግረው ”በገጠሪቱ ኢትዮጵያ 28 ሺህ አባወራዎችን ኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግም እየሰራን ነው” ብለዋል።

የኢትዮጵያን  የልማት ዕቅዶች ማገዝ በሚያስችሉ እንደ ግብርና በመሳሰሉ ዘርፎች በስፋት መሳተፍ ደግሞ የኮርፖሬሽኑ የወደፊት ዕቅድ መሆኑን አመልክተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በዚሁ ጊዜ ኮርፖሬሽኑ ከጀመራቸው የልማት ሥራዎች በተጫማሪ በአዳዲስ መስኮች ተሳትፎ እንዲያደርግ መጠየቃቸውን ውይይቱን የተከታተሉት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ ገልጸዋል።

በመጪዎቹ አራት ዓመታት ውስጥ ሥራው እንደሚጠናቀቅ የሚጠበቀው ይኸው ፕሮጀክት ለአገሪቷ የውጭ ምንዛሪ እንደሚያስገኝ ተስፋ ተጥሎበታል።

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ 2013 ኮርፖሬሽኑ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ባደረገው ስምምነት መሰረት በኦጋዴን በነዳጅ ፍለጋና ልማት ዘርፍ ተሰማርቶ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy