Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የደም ግፊት 10 መንስኤዎች

0 7,313

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የደም ግፊት 10 መንስኤዎች

 

የልብ በሽታ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቁ እና ድምፅ አልባ ገዳይ ከሆኑ በሽታዎች አንዱ ነው፡፡ የደም ግፊት (ወይም ከፍተኛ የደም ግፊት) ማለት ደም ልባችን በከፍተኛ ግፊት በደም ቧንቧዎች አማካኝነት ወደሌላው የሰውነት ክፍል ሲረጭ ነው ይህም ከተለመደው የደም መርጨት ተግባር በላይ ሲሆን ይከሰታል፡፡ ይህ ያልተለመደ የደም ግፊት ልብ ላይ ውጥረት በመፍጠር ያለጊዜ ሞት መንስኤ ይሆናል፡፡

1/ የጨው መብዛት አንዱ መንሰኤ ነው የአሜሪካ የልብ ማኅበር እንደገለጸው, ጨው (ወይም በቀን ከ 1,500 ሚሊ ግራም መውሰድ), ከመጠን ያለፈ መውሰድ ከፍተኛ የደም ግፊት, የስኳር በሽታ, እንዲሁም የልብና በሽታዎች-በየትኛውም ዕድሜ ላይ, ሊያስከትል ይችላል.

2 / የእድሜ ጣራ ሌላው መንስኤ ነው ሰወች በዕድሜ,ሲገፉ የደም ግፊት በተፈጥሮ ይጨምራል. ሆኖም ግን, ጥሩ ያልሆነ የአመጋገብ ሥርዓት, ከመጠን በላይ መጠጣት, ወይም ስብ እና ስኳር የበዛባቸው ምግቦች, ዕድሜ ጋር ከፍተኛ የደም ግፊት እንዲከሰት ምክንያት ይሆናል፡፡

3/ በእንቅልፍ ወቅት የአየር ማጣት መንስኤ ነው በእንቅልፍ ወቅት የኦክስጅን መጠን ማነስ የልብና የደም ዝውውር ሥርዓት ላይ ችግር የሚፈጥር ሲሆን አየር በደንብ ለማግኘት በሚያስችል ሁኔታ መተኛት ይመከራል

4/ ውፍረት ሌላው መሰረታዊ መንስኤ ነው ውፍረት ጋር የተያያዘ የደም ግፊት ችግር የሚከሰት ሲሆን የምንመገበውን ፕሮቲን ምግቦች መቀነስ ይመከራል

5/ ለእስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ማድረግ የማያስችል ህይወት ሌላው መንስኤ ነው፡፡ ሰዎች ቢያንስ ቢያንስ ለተወሰኑ ደይቃዎች መንቀሳቀስ ይኖርባቸዋል ሲል ይመክራል

6/ እጾች እና አልኮል መንስኤ ናቸው የአልኮል መጠጥ ከመጠን በላይ መውሰድ ወይም ለመዝናናት ዕፅ መጠቀም ልብ እና የደም ቧንቧዎች ላይ ውጥረት እና ጉዳት ያስከትላል.

7/ ጣፋጭ ምግብ የተለያዩ ጣፋጭነት ያላቸውን ምግቦች አዘውትሮ መመገብ ለበሽታው ያጋልጣል፡፡

8 ሲጋራ ማጨስ ሌላው ምክንት ሲሆን ሲጋራ ባለማጨስ ወይም ከሚጨስባቸው ቦታወች በመራቅ መከላከል ይቻላል፡፡

9. የሆርሞን ሁኔታዎች አንዳንድ የሆርሞን በሽታወች በተለይ ኩሺንግ ሲንድሮም የስቴሮይድ ሆርሞኖች ይበልጥ በሰውነት ውስጥ እንዲፈጠሩ ያደርጋል ይህም ለደም ግፊት በሽታ ያጋልጣል፡፡

10. የኩላሊት በሽታ ሌላው ምክንያት ነው የደም ግፊት አንዱ ዋነኛ ምክንያት የኩላሊት ህመም ነው

ምንጭ፡- አክቲቪ ቢት

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy